አትሌት ፅጌ ዱጉማና አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በውድድሩ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝተዋል
በ19ኛው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም አምስተኛ በመሆን አጠናቃለች።
በእንግሊዝ ግላስጎ ሲካሄድ የቆየው የ2024 የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ፍጻሜውን አግኝቷል።
ከየካቲት 22 እስክ 24 2016 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሻምፒዮና ከ130 በላይ ሀገራ የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ መሳተፋቸው ተነግሯል።
ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር በሴትና በወንድ በአጠቃላይ በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች መሳተፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በሻምፒዮናው በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ፣ በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ሆነዋል።
በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎች በማግኘት በሜዳልያ ሰንጠረዥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች ።
በሻምፒዮናው አሜሪካ 6 የወርቅ፣ 9 የብር እና 5 የነሃስ በድምሩ በ20 ሜዳያዎች በማግኘት ከዓለም አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
ቤሌጂየም በ3 የወርቅ እና አንድ የነሃስ በድምሩ በ4 ሜዳያዎች 2ኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ኒውዚላድ በ2 የወርቅ እና 2 የብር ሜዳሊያዎች 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።