ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከ2 ወራት በፊት በተወካዮች ም/ቤት ቀርበው ኢትዮጵያ ኢምባሲዎቿን በግማሽ ትቀንሳለች ብለው ነበር
በአልጀሪያ ፤አልጀርስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው ኢምባሲው ከፈረንጆቹ ጥቅምት 10 ቀን 2021 ጀምሮ ይዘጋል፡፡
ኢምባሲው የሚዘጋው የኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት በተፈጠረው የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እንደገና ለማደራጀት መንግስት በመወሰኑ እንደሆነም ኢምባሲው አስታውቋል።ይሁንና ኢምባሲው የሚዘጋው በጊዜያዊነት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተጎዳው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሲስተካከል ኢምባሲው ዳግም እንደሚከፈትም ተገልጿል።
እስከዚያው ድረስም የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ስራዎች ከአዲስ አበባ እንደሚከናወኑም ተገልጿል።
የኢምባሲው መዘጋት በኢትዮጵያ እና አልጀሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጎን እንደሌለም ኢምባሲው በመግለጫው ገልጿል።
የአልጅሪያ ኢምባሲ በተጨምሪ ሌሎች የሚዘጉ ኢምባሲዎችና ቆንስላዎች መኖራቸውን የውጭ ጉዳይ ምንጮች ለአል ዐይን ኒውስ ገልጸል፡፡
ከሁለት ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትይጵያ በተለያዩ ሀገራት የከፈተቻቸውን ኢምባሲዎች የመቀነስ እቅድ አንዳላት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
“ከ60 የሚልበጡ ኤምባሲዎች መኖራቸው ለኢትዮጵያ ጠቅሞ እንደ ሆነ መመልከት ያስፈልጋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢያንስ 30 ኤምባሲ ልትቀንስ እንደምትችልም ተናግርው ነበር፡፡
አንዳንዶቹ ኤምባሲዎች ተዘግተው አምባሳደሮቹ እንደ አስፈላጊነቱ ወደየተሾሙበት ሀገር በቀጠሮ ቢሄዱ ይሻላል ያሉ ሲሆን፤ በውጭ በገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራዎችን ማለታቸውም ይታወሳል፡፡