በኢራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ጥቃት ደረሰበት
በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የሚገኘዉ የአሜሪካ ኢምባሲ በሶስት ሮኬቶ ጥቃት የደረሰበት ሲሆን፣ ጥቃቱ በአንድ ስዉ ላይ ጉዳት ማድረሱን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደተናገሩት ከሆነ በግለሰቡ ላይ የደረሰዉ ጥቃት ቀላል እንደሆነና ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ስራ መመለሱን ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሞርጋን ኦርታገስ ጥቃቱ መድረሱን ቢገልጹም፤ አሜሪካ ኢምበሲ ላይ መሆኑን በቀጥታ አልገለጹም፡፡
ኦርታገስ ኢራቅ የአሜሪካን ኢምባሲና ዲፕሎማቶችን በመጠበቅ ኃላፊነቷን እንድትወጣ ጥሪ ቅርበዋል፡፡
አሜሪካ ለጥቃቱ ኢራንን በቀጥታ ባትወቅስም፣ በአካባቢው ኢራን የጸጥታ ስጋት መሆኗን ከዚህ በፊት ያደረሰችውን ጥቃት በማንሳት ገልፃለች፡፡
ሞርጋን ኦርታገስ “የጸጥታው ሁኔታ አሁን ዉጥተረት ላይ ነው፤ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች የስጋት ምንጭ ናቸው፤ ስለዚህ ንቁ መሆን አለብን” ብለዋል፡፡
ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በአሜሪካ ወታደራዊ ዘመቻ የኢራኑ ጄነራል ቃሲም ሱሌማኒ በኢራቅ ምድር ከተገደሉ በኋላ በአሜሪካና በኢራን መካከል ያለው
ዉጥረት ብሏል፡፡
ኢራንም ይህን ተከትሎ በኢራቅ ሰፍረው በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ሚሳል በመተኮስ አጸፋዊ እርምጃ መውሰዷም የሚታወስ ነው፡፡