በኢትዮጵያ በጎግል ላይ ሰዎች በብዛት የፈለጉት ቃላቶች የትኞቹ ናቸው?
ጎግል በዓመቱ በብዛት የተፈለጉ ቃላቶችን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በኢትዮያ በብዛት የተፈለጉትም ተካተዋል
በኢትዮጵያ በ2024 ጎግል ላይ ከተፈለጉ ቃላቶች ውስጥ ኢትዮጵያ (Ethiopia) የሚለው ቃል ዘንድሮም ቀዳሚ ነው
ጎግል በፈረንጆቹ 2024 ሰዎች በድረ ገጹ ላይ በመግባት በብዛት የፈረጉትን (ሰርች) ያደረጉትን ቃላቶች ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ በብዛት ጎግል ላይ ከተፈለጉ ቃላቶች ውስጥም ኢትዮጵያ (Ethiopia) የሚለው ቃል ቀዳሚ ነው የተባለ ሲሆን፤ ዩ ትዩብ (youtube) እና ትራንስሌት (Translate) የሚለው ቃል ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
ጎግል (Google) የሚለውን ቃል በራሱ በጎግል ላይ በመፈለግም በኢትዮጵያ በብዛት ከፈለጉ ቃላቶች ውስጥ 4ኛ ደረጃን ይዟል።
በ2024 በኢትዮጵያ በጎግል ላይ በብዛት የተፈለጉ ቃላቶች
1 ኢትዮጵያ (Ethiopia)
2 ዩ ትዩብ (youtube)
3 ትራንስሌት (Translate)
4 ጎግል (Google)
5 አፕ (app)
6 ዌዘር (weather)
7 ፕሪምየር ሊግ (premier league)
8 ቴሌግራም (telegram)
9 ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ (amharic to English)
10 ቤስት ቤት (best bet)
11 አርሰናል (arsenal)
12 ፌስቡክ (facebook)
13 ጎግል ትራንስሌት (google translate)
14 ቲክቶክ (tiktok)
15 ሊቨርፑል (Liverpool)