በጎግል ማፕ ምክንያት ባሏ የሞተባት ሚስት ጎግልን ከሰሰች
በአሜሪካ አንድ ግለሰብ ጎግል ማፕን በመጠቀም ወደ ተደረመሰ ድልድይ ገብቶ ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል
ጎግል በበኩሉ በተፈጠረው አደጋ ማዘኑን ገልጾ የተመሰረተበትን ክስ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል
በጎግል ማፕ ምክንያት ባሏ የሞተባት ሚስት ጎግልን ከሰሰች
ንብረትነቱ የአልፋቤት ኩባንያ የሆነው ጎግል ለመንገደኞች አቅጣጫን ማሳየት አላማው ያደረገ መተግበሪያ አለው።
በአለማችን በርካቶች ይህንን አቅጣጫ መጠቆሚያ መተግበሪያ በመጠቀም ላይ ሲሆኑ በአሜሪካ ግን ጎግል ማፕ ለሰው ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
እንደ ኤፒ ዘገባ ከሆነ ፊሊፕ ፓክሰን የተባለ አሜሪካዊ ጎግል ማፕን ተጠቅሞ ወደ ቤቱ እያመራ እያለ ለአደጋ ተግጋልጦ ህይወቱ አልፏል።
የልጁን ልደት አክብሮ እየተመለሰ የነበረው ፊሊፕ ጎግል ማፕን ተጠቅሞ እየተጓዘ እያለ ከስድስት ዓመት በፊት በአደጋ ምክንያት በተደረመሰ ድልድይ ውስጥ ገብቷል ተብሏል።
ጎግል ማፕ ይህ መንገድ ብልሽት እንደሌለበት አድርጎ ለደንበኞቹ መናገሩ ለአደጋው ምክንያት ሆኗል በሚልም በኩባንያው ላይ ክስ ተመስርቶበታል።
የፊሊፕስ ባለቤት ለኤፒ እንዳለችው " ልጆቼ አባታቸው እንዴት እና በምን ምክንያት እንደሞተ ያውቃሉ፣ ይህ ቀላል ነገር እንዴት ለሰው ህይወት ማለፍ ምክንያት ሊሆን ቻለ" የሚለው ነገር ያሳዝናል ብላለች።
ጎግል ይህ ለሰው ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው ድልድይ መደርመሱን ከዚህ በፊት ያውቅ ነበር የተባለ ሲሆን ብልሽቱን እያወቀ መረጃውን አለማስተካከሉ እንደ ጥፋት ታይቶ ክስ ሊመሰረትበት መቻሉ ተገልጿል።
ጎግል ኩባንያ በበኩሉ ለደረሰው አደጋ እና ህይወት ማለፍ ማዘኑን አስታውቋል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጆሴ ካስታኔዳ እንዳሉት በጎግል ላይ በቀረበበው ክስ ጉዳይ ዙሪያ በፍርድ ቤት ተገኝቶ ምላሽ ለመስጠት እየተወያየ መሆኑንም ገልጻል።