የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ተደረገ
በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ምደባቸውን መመልከት ይችላሉ
ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል
በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ተደረገ።
በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለምትከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከዛሬ ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የመመልከቻ አማራጮቹም፤
Website: https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot
በተያያዘ ዜና የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።
በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 255
የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 -234
የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600- 218
የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 200
ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 224
ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210
ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 192
ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180
አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700- 210
አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700- 210
አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 - 180
አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 - 180
ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 -150 ያመጡ
ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 -150 እና ከዚያ በላይ ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።