ወደ ዩኒቨርሲቲ ያልገቡ ተማሪዎች ባሉበት እንዲቆ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
መንገድ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከመነሻቸው እና ከመድረሻቸው ወደ ሚቀርባቸው እንዲሔዱ ሚኒስቴሩ መክሯል
ሚኒስቴሩ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎች በጊቢያቸው እንዲቆዩ አሳስቧል
ወደ ዩኒቨርሲቲ ያልገቡ ተማሪዎች ባሉበት እንዲቆ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠል ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ተማሪዎቻቸውን ጠርተው በመቀበል ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ አሁን በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ መግታት አስፈላጊ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት እስከ አሁን ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው የደረሱ ተማሪዎች በጊቢያቸው እንዲቆዩና ከተቋሞቻቸው ኃላፊዎች የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያ እየተከታተሉ እንዲንቀሳቀሱ ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል፡፡
በጉዞ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ወደ እንደየቅርበቱ ሁኔታ ወደ ላጆቻቸው (ወደ መነሻቸው) እንዲመለሱ ወይም ወደ ተቋማቸው እንዲሄዱ ነው ሚኒስቴሩ ምክረኀ-ሀሳብ ያቀረበው፡፡
እስካሁን ከመኖሪያ አካባቢያቸው (ከሚገኙበት ስፍራ) ያልተነሱ ተማሪዎች ደግሞ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ በሚኖሩበት እንዲቆዩ አሳስቧል፡፡
ሁሉም ተቋማት በቂ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጸው፡፡
መረጃዎችን በየወቅቱ እንደሚሰጥ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ ተማሪዎች ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች የሚሰጡ መረጃዎችን እና ማስታወቂያዎችን ብቻ እንዲከታተሉ አሳስቧል፡፡