ፖለቲካ
የአየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ
ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል
ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ ከሃላፊነት ተነስተዋል
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።
ሌተናል ጄነራል ይልማ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩትን አቶ ግርማ ዋቄን በመተካት ነው የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢነት መሾማቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል።
ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ከሰኔ 1 2015 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውንም ነው አየር መንገዱ ያስታወቀው።
ሌተናል ጄነራል ይልማ ላለፉት ሁለት ዓመት ከመንፈቅ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
አቶ ግርማ ዋቄ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ባገለገሉባቸው ጊዜያት በዘርፉ የነበራቸውን የካበተ ልምድ ለተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ሲያካፍሉ መቆየታቸውንም አየር መንገዱ በመግለጫው አስታውቋል።