ሙሉቀን መለሰ የሙዚቃ ስራን በማቆም በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ሲሰራ እንደነበር ይታወሳል
አንጋፋው ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ ባደረባት ሕመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ በ70 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ በአደረበት ህመም ለረጅም ጊዜ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ70 ዓመቱ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በ1966 ዓ.ም በ12 አመቱ የሙዚቃ ስራውን በምሽት ክለቦች እና በምሽት ክለብ ባለቤቶች በተቋቋሙ ቡድኖች በመዝፈን የጀመረ ሲሆን፤ ወደ አስር የሚጠጉ የሙሉቀን መለስ የሙዚቃ ስራዎች በሸክላ የታመዋል።
ከሙሉቀን መለሰ ተወዳጅ ዘፈኖች መካከልም “ሰውነቷ፣ ሆዴ ነው ጠላትሽ፣ መውደዴን ወደድኩት፣ ይረገም ለቤ፣ ሌቦ ነይ፣ቼ በለው እና ውቢት ” የተሰኙት ተጠቃሽ ናቸው።
ሙሉቀን ከአራ አስርት ዓመታት በፊት ወደ በሀገረ አሜሪካ በማቅና ኑሮውን በዚያ በመምራ ላይ የነበረ ሲሆን፤ በሀይማኖቱ ምክንያት ከሙዚቃ ዓለም እራሱን አግልሏል።
ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ የሙዚቃ ስራን ካቆ በኋላም በወንጌላውያን አማኞች ቤተክርስትያን ዘማሪ በመሆን አገልግሏል።
ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር ዳማ ኪዳነምህረት በምትባል መንደር በ1946 ዓ, ም ተወለደ የህይወት ታኩ ያሳያል።