ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአካል ብቃት አሰልጣኝ በአንድ ቀን ውስጥ ሁለት የዓለም ክብረወሰኖችን ሰበረ
ሀብታሙ በአንድ ሰዓት ውስጥ በርካታ በርፒ በመስራት በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ስሙ ሰፍሯል
የአካል ብቃት አሰልጣኙ ከዚህ ከቀደም የተሰበረበትን ክብረወሰን መልሶ በእጁ አስገብቷል
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአካል ብቃት አሰልጣኝ በአንድ ቀን ውስጥ ሁለት ክብረወኖችን በመስበር በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ስሙ ሰፍሯል።
አባቱን በጦርነት ያጣውና ገና የሁለት ዓመት ህጻን እያለ እናቱንም በሞት ያጣው ሀብታሙ ፈንክሬ፤ ወደ ሆላንድ በጉዲፈቻ ተወስዶ ነበር ያደረገው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሀብታሙ በኔዘርላንድ ውስጥ ህይወቱን በተሻለ መንገድ ለመምራት የግል አሰልጣኝ፣ የስነ-ምግብ ባለሙያ እና የአእምሮ አሰልጣኝ በመሆን እየሰራ ይገኛል።
ሀብታሙ አሁን ላይ የዓለም ክብረወሰኖች ባለቤት መሆን መቻሉ ተነግሯል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአካል ብቃት አሰልጣኝ ሀብታሙ ከሰሞኑ በአንድ ቀን ውስጥ ሁለት የዓለም ክብረወሰኖችን በመስበር በጊነስ ወርልድ ሪከርዶች ስሙን ማስፈርም ችሏል።
ሀብታሙ በመጀመሪያ የሰበረው የዓለም ሪከርድ ከደረት ወደ መሬት የሚሰራ በርፒ ሲሆን፤ በዚህም በሶስት ደቂቃ ውስጥ 81 በርፒ በመስራት ከዚህ ቀደም በ77 በርፒ ተያዘውን ሪከርድ ሰብሯል።
በመቀጠልም ሁለተኛውን የዓለም ክብረወሰን በአንድ ሰዓት ውስጥ በርካታ በርፒ በመስራ የሰበረ ሲሆን፤ በዚህም ሀብታሙ በአንድ ሰዓት ውስጥ 1 ሺህ 10 በርፒ በመስራ ከዚህ በበፊት በ1 ሺህ 2 ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በእጁ ማስገባት ችሏል።
የአካል ብቃት አሰልጣኝ ሀብታሙ ሶስተኛውን በአንድ ቀን ሶስተኛውን ክብረወሰን ለመስበር በአንድ ደቂቃ በርካታ በርፒ ለመስራ ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለትም ተነገሯል።
"በርፒ ካሉት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ውስጥ በጣም ከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው” ያሉ ሀብታሙ፤ "በርፒስ መስራት ስችል ሌላ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እችላለሁ" ብሏል።
ሀብታሙ ይህንን ሪከርድ ባለፈው አመት 986 በእጁ ማስገባት ችሎ የነበረ ቢሆንም፤ ሁለት ጊዜ ተሰብሮበት ነበር። በመጨረሻ በርትቶ በመስራት ክብረወሰኑን መልሶ በእጁ አስገብቷል።
“እዚህ የመጣሁት ሶስት በጊነስ ወርልድ ሪከርድ ክብረወሰኖችን ለመስበር ነበር” ያለው ሀብታሙ፤ “አሁን ሁለቱን አሳክቻለሁ በሚቀጥለው ዓመት ሶስተኛውንም በእጄ አስገባለሁ” ሲል ተናግሯል።