የፋይናንስ ተቋማቱ የሚሰጡት የብድርና ሌሎች አገልግሎትም እየጨመረ ነው ተብሏል
በኢትዮጵያ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ቁጥር በየጊዜው እድገት እያሳየ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የንግድ ባንኮች ቁጥር 31 የደረሰ ሲሆን፥ የክፍያ እና የሞባይል ዋሌት አገልግሎት የሚሰጡ ከ13 በላይ ተቋማትም ወደ ስራ ገብተዋል።
የፋይናንስ ተቋማቱ አጠቃላይ ብዛት ከ100 በላይ ቢደርስም የሚሰጡት ብድር ግን ውስን ነው።
ባንኮች እስካሁን የሰጡት ብድር ቢታይ ከ500 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳልቻሉም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለህዝብ እንደራሴዎች ባደረጉት ገለጻ ላይ ጠቅሰዋል።
ለተመሳሳይ እና አቅም ላላቸው ሰዎች ብቻ ሲሰጥ የነበረውን ብድር ተደራሽነት ለማስፋትና የአርሶአደሮችን የብድር ተጠቃሚነት ለማሳደግም እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች በሞባይል 7 ቢሊየን ብር ብድር ማግኘታቸውም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በገላጭ ምስል ይመልከቱ፦