በአራት ክልሎች የተደረገው የድጋሚና ቀሪ ምርጫ ሂደት መጠናቀቁን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
ምርጫው በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ነው የተካሄደው
ምርጫ ሂደቱ በአራቱም ክልሎች በ29 የምርጫ ክልሎችና በ1 ሺህ 218 የምርጫ ጣቢያዎች ተካሂዷል
በአራት ክልሎች የተደረገው የድጋሚና ቀሪ ምርጫ ሂደት በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በትናንትናወረ ዕለት ተካሂዷል።
አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት በተመለከተም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ መግለጫ ሰጥተዋል።
በ6ኛ ዙር ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በፀጥታና በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄዱ በቀሩ ክልሎች በትናንትናው እለት ምርጫ መከናወኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የምርጫ ሂደቱን ነፃ፣ ገለልተኛና ተአማኒ ለማድረግ ቀደም ብሎ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው የቀሪና ድጋሚ ምርጫ ሂደቱ በአራቱ ክልሎች በ29 የምርጫ ክልሎች እና በ1 ሺህ 218 የምርጫ ጣቢያዎች መካሄዱን ገልፀዋል።
በሁለት ምርጫ ጣቢያዎቾ ግን የምርጫ ቁሳቁስ ዘግይቶ በመድረሱ ለዛሬ መተላለፉንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አስታውቀዋል
የምርጫ ሂደቱ ከጥዋቱ 12 ጀምሮ ድምፅ ሲሰጥ መዋሉን ገልፀው በመተከል ዞን ዳንጉር ምርጫ ጣቢያ ከነበሩ በ33 ጣቢዎች መካከል በሁለቱ ምርጫ ጣቢያዎች በቁሳቁስ መዘግየት ሳቢያ ለነገ መተላለፉን ገልፀዋል።
በአንድ ምርጫ ጣቢያ ተመሳሳይ እና ስም ያልተፃፈባቸው መታወቂዎች ተገኝተው ማጣራት ተደርጎ እርምጃ መወሰዱንም ጠቅሰዋል።
ድምፅ በተሰጠባቸው በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ቆጠራ ላይ ሲሆኑ የተወሰኑት ላይ ደግሞ ወደ ምርጫ ክልል ተወስደው እንዲቆጠሩ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በተያያዘ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 40 የምርጫ ጣቢያዎች የፀጥታ ችግር በመኖሩ በትናትናው ዕለት ድምፅ ሳይሰጥ መቅረቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ባሳለፍነው ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ ላይ፤ የፀጥታ ችግሮች ባለመስተካከላቸው አሁንም ምርጫ የማይደረግባቸው አካባቢዎች መኖራቸውም ተነስቷል።
አስቻይ ሁኔታዎች ሲኖሩ የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተቀሩ ቦታዎች ምርጫ ለማካሔድ ቦርዱ ይሰራል ተብሏል።