የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ይሰጣል ተባለ
ፈተናው በተባለው ዕለት በትግራይ ክልል አይሰጥም ተብሏል
ይህ አገር አቀፍ ፈተና በ2 ሺህ 112 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ተገልጿል
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 እንደሚሰጥ ተገለጸ።
በኮሮና ቫይረስ ጉዳት ምከንያት የተራዘመው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 12 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ እንዳስታወቀው የ2013 ዓመተ ምህረት የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ወደ ዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለአራት ቀናት ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን ገልጿል።
የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በሰጡት መግለጫ በዚህ ፈተና ላይ ከ618 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን አንደሚወስዱ ተናግረዋል።
ፈተናውን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለመከወን 16 ሺህ ፋታኝ መምህራን እና 2 ሺህ 112 የፈተና ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል ዶክተር ዲላሞ።
የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች እንደሚሰጥም ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል።