ልዩልዩ
በ70 ዓመታቸው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱት የጉጂ ዞን አዛውንት
ለትምህርት ካላቸው ፍላጎት እና ፍቅር የተነሳ ፈተናውን መውሰዳቸውን አዛውንቱ ተናረዋል
በኦሮሚያ ክልል በዘንድሮ 481 ሺህ 294 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ወስደዋል
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ነዋሪ የሆኑት የ70 ዓመቱ አዛውንት የዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መውሰዳቸው ተነግሯል።
አዘውንቱ ሃሮ ቡሉልታ የሚባሉ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የጎሮ ዶላ ወረዳ ነዋሪ ናቸው።
የ70 ዓመቱ አዛውንት ሃሮ ቡሉልታ በኦሮሚያ ክልል ከሰኔ 8 2013 ዓ.ም ጀምሮ በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ላይ መቀመጣቸው ተነግሯል።
አዛውንቱ ሃሮ ቡሉልታ በጎሮ ዶላ ወረዳ በሚገኝ ጉዱባ ቡሩር ትምህረት ቤት ፈተናውን መውሰዳቸውም ተነግሯል።
በፈተናው ላይ ሊቀመጡ የቻሉትም ለትምህርት ካላቸው ፍላጎት እና ፍቅር የተነሳ እንደሆነ መናገራቸውንም የጎሮ ዶላ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 10 2013 ዓ.ም ለ3 ቀናት መሰጠቱ ይታወቃል።
በዘንድሮው ትምህርት ዘመን በኦሮሚያ ክልል 481 ሺህ 294 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መውሰዳቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።