ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር በካይሮ ተወያዩ
ውይይታቸውም በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበረ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል
የሱዳን ጎረቤት ሀገራት በወቅታዊ የሱዳን ሁኔታ ላይ ዛሬ በግብጽ የወያያሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታሕ አልሲሲ ጋር በካይሮ ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውይይታቸውን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት "በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር ውይይቶች አካሂደናል” ብለዋል።
ውይይታቸውም ውይይታቸውም በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበረ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታል ኤልሲሲ ባሳለፍነው ወር በፈረንሳይ ፓሪስ መገናኘታቸው ይታወሳል።
መሪዎቹ በአለማቀፉ የፋይናንስ ጉባኤ ላይ ነው ከአንድ አመት በኋላ በአካል የተገናኙት።
ኢትዮጵያ እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል ዙሪያ በተለያየ ጊዜ በሚሰጧቸው መግለጫዎች ግንኙነታቸው የተካረረ ቢመስልም መሪዎቹ በፈገግታ ታጅበው ሲጨባበጡ ታይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን እንደመጡ በግብጽ ጉብኝት ማድረጋቸውና ኢትዮጵያ የምትገነባው የህዳሴ ግድብ ግብጻውያንን እንደማይጎዳ መናገራቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባሳለፍነው ሳምንት በፓርላማ ባደረጉት ንግግርም የዘንድሮ የህዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ ውሃ የሚይዘው ግብጽ እና ሱዳን በቂ ውሃ መያዛቸውን ካረጋገጥን በኋላ ነው ማለታቸው አይዘነጋም።
በዚህም ምክንያት ከዚህ ቀከድመ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ይከናወን የነበረው የህዳሴ ግድብ ውሃ ሜዝ እስከ መስከረም መራዘሙንም ገልጸዋል።