ፖለቲካ
በድሬዳዋ ከተማ የ'5ጂ' ኔትወርክ ማስጀመሩን ኢትዮቴሌኮም አስታወቀ
ኢትዮቴሌኮም በ2016 የመጀመሪያ መንፈቅ አመት 42.86 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 98 በመቶ ማሳከቱን ገልጿል
ኢትዮቴሌኮም ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ በአዳማ እና በጅግጅጋ ከተሞች የ5ጂ የኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሩ ይታወሳል
በድሬዳዋ ከተማ የ'5ጂ' ኔትወርክ ማስጀመሩን ኢትዮቴሌኮም አስታወቀ።
በድሬዳዋ ከተማ የ'5ጂ' ኔትወርክ ወይም የአምስተኛ ትውልድ ሞባይል ኔትወርክ ማስጀመሩን አስታውቋል።
ኢትዮቴሌኮም በፊስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ በዛሬው እለት የ'5ጂ' ኔትወርክ አገልግሎት በድሬዳዋ ጀምሯል።
ኢትዮቴሌኮም ቀደም ሲል በአዲስ አበባ፣ በአዳማ እና በጅግጅጋ ከተሞች አሁን ላይ በአለም የመጨረሻ የሆነውን ፈጣን የ5ጂ የኔትወርክ አገልግሎት ማስጀመሩ ይታወሳል።
የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶች በተለይም ከግጭት ጋር በተያያዘ በበርካታ አካባቢዎች አገልግሎቱ ሲቋረጡ ይሰተዋላል።
ይሁን እንጂ ትርፋማ ሆኖ መቀጠሉን በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
ኢትዮቴሌኮም በ2016 የመጀመሪያ መንፈቅ አመት የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 74.6 ሚሊዮን ከፍ ማድረጉን እና 42.86 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 98 በመቶ ማሳከቱን ገልጿል።
የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ ዘርፎች 84.7 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን የገለጸው ኢትዮቴሌኮም እና ይህም የእቅዱን 109 በመቶ ይሸፍናል ብሏል።