ቡርኪናፋሶ ለተበረከተላት "የስንዴ ስጦታ" ሩሲያን አመሰገነች
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ባለፈው አመት በሴንትፒተርስበርግ በተደረገ ስብሰባ ለቡርኪናፋሶ ሰንድ እንደሚሰጡ ቃል ገብተው ነበር
በፈረንጆቹ 2022 መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደ ወዲህ በሞስኮ እና በኡጋድጉ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንክሯል
ቡርኪናፋሶ ለተበረከተላት "የስንዴ ስጦታ" ሩሲያን አመሰገነች
ሀጀሪቱ ከሩሲያ 25ሺ ቶን ሰንዴ መቀበሏን አስታውቃለች።
ሀገሪቱ ስንዴውን መረከቧን ያረጋገጡ አንድ ሚኒስትር "ውድ ስጦታ" ሲሉ ገልጸውታል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ባለፈው አመት በሴንትፒተርስበርግ በተደረገ ስብሰባ ለቡርኪናፋሶ ሰንድ እንደሚሰጡ ቃል ገብተው ነበር።
ሩሲያ በአለም ቀዳሚ ከሚባሉት ሰንዴ አምራች ሀገራት አንዷ ስትሆን በዚህ አመት 45 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ወደ ውጭ ትልካለች ተብሎ ይጠበቃል።
በፈረንጆቹ 2022 መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደ ወዲህ በሞስኮ እና በኡጋድጉ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንክሯል።
ሩሲያ ከሶቬት ህብረት መውደቅ ጀምሮ የተዘጋውን ኢምባሲዋን ባለፈው ወር ከፍታለች።
ቡርኪናፋሶም በተመሳሳይ ሁኔታ የቀድሞ ቅኝ ገዥዋን ወታደሮች በማስወጣት ከፈረንሳይ ጋር ያላትን ግንኙነት እያላላች ትገኛለች።
በሀገሪቱ ተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጥምረት የሆነው ኢኮዋስ ህገመንግስታዊ ያልሆነ የመንግስት ለውጥ ባደረጉት ወታሮች ላይ ጫና ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ወታደራዊ ጁንታው ስልጣን ሲይዝ እስላማዊ አማጺያንን እንደሚቆጣጠር ቃል ቢገባም፣ የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሊረጋጋ አልቻለም።
ባለፈው ሳምንት ሩሲያ የሀገሪቱን ወታደራዊ መሪ ኢብራሂም ትራኦሬን እና የሀገሪቱን ህዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ 100 ወታደሮችኔ ወደ ኡጋድጉ መላኳን የሚያሳይ ሪፖርት መውጣቱ ይታወሳል።