ህብረቱ "ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም" በማለት ታዛቢ የመላክ እቅዱን ሰርዟል
የህብረቱ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦረል አውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች እንዲልክ በማሰብ ለመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ አስፈላጊ ናቸው በተባሉ ቁልፍ መስፈርቶች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከስምምነት ለመድረስ ጥረት ሲያደረግ ቢቆይም አልተቻለም ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል "ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም " ስለዚህም የታዛቢ ልኡክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊያደርግ የነበረው ስምሪት መሰረዝ አለበትም ነው ያሉት የህብረቱ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦረል፡፡
የምርጫ ታዛቢዎች ተልዕኮ የአውሮፓ ህብረት ለዴሞክራሲ በሚዳረገው ድጋፍ ቁልፍ ነው የሚል ጠንካራ እምነት አለው ነው ፡፡
ማንኛውም የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሊያሟላቸው የሚገቡ ነገሮች ማለትም የልኡኩ ነፃነት እና የደህንነት ስጋቶች በሚኖሩበት ጊዜ የልኡኩ የግንኙነት ስርዓቶች እንዲሁም ልኡኩ የሚጠቀምባቸው የደህንነት ቁሳቁሶች ማስመጣት የመሳሰሉ መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ ባለመፈቀዱ ባለመቀበላቸው የአውሮፓ ህብረት ቁጭት ይሰማዋል፡፡
ህብረቱ ምርጫውን ለመታዘብ ማረጋገጫ ባለማግኘቱ፣ ዲሞክራሲ ለሚፈልገው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ባለማረጉ ቅር መሰኘቱን ገልጿል፡፡ ህብረቱ የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያውያ ህጋዊ የፖለቲካና የሲቪል መብታቸውን እንዲያራምዱ ዋስታና እንዲሰጥ ያበረታታል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያን ምርጫ ታአማኒ፣አካታችና ግልጽ ምርጫ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የ20 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ ማድረጉን አውሮፓ ህብረት አስታውሷል፡፡
መንግስትን የሚመራው ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑትና የምርጫ ዘርፍ ኃላፊ ዛዲግ አብረሃ ከወራት በፊት ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃል-ምልልስ ምርጫ 2013 ማንኛውም አካል መታዛብ እንደሚችል ገልጸው ነበር፡፡
የአውሮፓ ህብረት እቅድ መሰረዝን ተከትሎ መንግስት እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡