የአውሮፓ ጦር መሳሪያ አምራች ኢንዱስትሪዎች የበለጠ መተባበር አለባቸው ተብሏል
አሜሪካ በእስያ ሀይሏን እያሰፋች መሄዷ ለአውሮፓ ስጋት ደቅኗል ተባለ፡፡
ሬን ሜታል የተሰኘው የጀርመኑ ጦር መሳሪያ አምራች ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አርሚን ፓፐርገር ስለ አውሮፓ ቀጣይ ስጋቶች ከፋይናንሺያል ታየምስ ጋር ሰፊ ቃለ መጠይቅ አድርገዋል፡፡
ስራ አስፈጻሚው በቃለ መጠይቁ ወቅት እንዳሉት የአውሮፓ መሪዎች በተለይም ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ አሜሪካ ለአውሮፓ ሀገራት ደህንነት ቅድሚያ ትሰጣለች ብለው ያምኑ ነበር፡፡
ይሁንና አሜሪካ ከአውሮፓ ይልቅ ለእስያ ሀገራት ቅድሚያ እንደምትሰጥ ተረጋግጧል ያሉት ስራ አስፈጻሚው ለዚህ ማሳያው ደግሞ ለዩክሬን የምትሰጠውን ጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቆሟን ነው፡፡
በተለይ ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ በቀጣህ ህዳር ወር ላይ በሚካሄደው ምርጫ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ አውሮፓዊያን ብቻቸውን እንደሆኑ የበለጠ ያውቁታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ሀገራት ጦር መሳሪያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለየብቻቸው ከመስራት ይልቅ በጋራ ወደ መስራት፣ አንዱ የሌለውን ሌላው እንዲያመርት እድል መስጠት እና ሀገራትም ለዚህ ትብብር እንዲያደርጉ ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በአውሮፓ ግዙፍ የሆነው ሬንሜታል የተሰኘው የጀርመኑ ጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያ የዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ትዕዛዝ እንደማይመጣለት አሁን ላይ ግን ስራ እንደበዛበት ተገልጿል፡፡
አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም ግምገማ ዙሪያ ምን አሉ?
ፋብሪካው ከዩክሬን ጦርነት በፊት በዓመት የማምረት አቅሙ 70 ሺህ የጦር መሳሪያ ብቻ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ አሀዙ ወደ 700 ሺህ ከፍ እንዳለለትም ተገልጿል፡፡
ስራ አስፈጻሚው አክለውም ፋብሪካቸው አንድ ቀን የጦር መሳሪያ ፍላጎት የሚጨምርበት ወቅት መምጣቱ አይቀርም በሚል አስቀድመው የፋብሪካውን የማምረት አቅም ሲያሳድጉ መቆየታቸውን፣ ከጀርመን ውጪም በአውስትራሊያ፣ ብሪታንያ እና ሀንጋሪ ተጨማሪ ፋብሪካዎችን ሲያዘጋጁ መቆየታቸውንም አክለዋል፡፡