ግብጽ ከአውሮፓ ህብረት 8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች
የገንዘብ ድጋፉ በሩሲያ ላይ የተመሰረተውን የአውሮፓ ነዳጅ ግብይት አማራጭን ለማስፋት እንደሚውል ተገልጿል
የአውሮፓ ህብረት ግብጽን እንደ ቁልፍ አጋር እንደሚያያት አስታውቋል
ግብጽ ከአውሮፓ ህብረት 8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች፡፡
ሰሜን አፍሪካዊቷ ግብጽ ከአውሮፓ ህብረት የ8 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍማግኘቷ ተገልጿል፡፡
ሮይተርስ የአውሮፓ ህብረት ቢሮን ጠቅሶ እንደዘገበው ህብረቱ እና ግብጽ ከያዝነው የፈረንጆቹ 2024 እስከ 2027 ድረስ የሚተገበር የሶስት ዓመት ትብብር ስምምነት ለመፈራረም ተስማምተዋል፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረት ህብረቱ ለግብጽ ኢኮኖሚ ድጋፍ 5 ቢሊዮን ዩሮ የሚሰጥ ሲሆን 600 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ፣ 1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላሩ ደግሞ ለመሰረተ ልማት ግንባታ ይውላል፡፡
ይህንን ስምምነት ለመፈራረምም የህብረቱ ኮሚሽነር ኡርሱላ ቮንደርሊን ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ኦስትሪያ፣ ቤሊጂየም፣ ሲፕረስ እና ግሪክ ባለስልጣናት ጋር ወደ ካይሮ እንደሚጓዙ ተገልጿል፡፡
ገብጽ ለአውሮፓ ህብረት ስጋት የሆኑትን ስደተኞችን መቆጣጠር፣ የሀይል አማራጭ በመሆን እና ባለመረጋጋት ውስጥ ያሉት ሱዳን፣ ሊቢያ እና ፍልስጤማዊን ስደተኞችን በመያዝ ዋነኛ አጋር ተብላላች፡፡
ግብጽ ገንዘቧን ካዳከመች ከሰአታት በኋላ ከአይኤምኤፍ ብድር አገኘች
ዘጠኝ ሚሊዮን ስደተኞችን እንዳስጠለለች የተገለጸው ግብጽ ተጨማሪ ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ እና ባሉበት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው በሚል ከህብረቱ የገንዘብ ድጋፍ እንደምታገኝ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሩሲያ ነዳጅ ላይ ጥገኛ የሆነችው አውሮፓን አማራጭ የነዳጅ ገበያ እንዲያገኙ ግብጽ ዋነኛ አጋር ተደርጋ እንደምትወሰድም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ግብጽ 164 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ ያለባት ሲሆን በኮሮና ቫይረስ፣ አለመረጋጋት እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ምክንያት የኢኮኖሚ መናጋት አጋጥሟታል፡፡