የአውሮፓ ህብረት በወሲብ ቅሌት ምክንያት ለድርጅቱ የኮንጎ ፕሮግራም የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ማቆሙን ገለጸ
ህብረቱ ድጋፉን ማቆሙ በድርጅቱ የሌ ሀገር ስራ ላይ ተጽእኖ እንደማይኖረው አስታውቋል
የአለም ጤና ድርጅት ሰራተኞቹ ሴቶችን በመድፈር ወንጀል መሳተፋቸው መረጋገጡንና እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቆ ነበር
የአውሮፓ ህብረት ለአለም ጤና ድርጅት የዲሞክራቲክ ሪፐብክ ኮንጎ ፕሮግራም የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ፣ ድርጅቱ የተፈጠረውን የወሲብ ቅሌት የያዘበት መንገድ ላይ ስጋት ስላለው ማቆሙን ሮይተር ዘግቧል፡፡
ሮይተርስ አየሁት ባለመው መረጃ መሰረት ለኢቦላና ለኮቪድ የሚደረጉ ድጋፎችን ጨምሮ ለአምስት መርሃ ግብሮች የሚያደርገውን ድጋፍ አቁሟል፡፡ ህብረቱ እንዳይሰጥ ያገደው የገንዘብ መጠን 20 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
ሮይተርስ መቀመጫወቅን ብራሰልስ ያደረገው ድርጅት፤ ሰጠኝ ባለው መልስ አጋር ድርጅቶች እንዲህ አይነት ተቀባይነት የሌለው ድርጊት እንዳይከሰት ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው፤ ድርጊቶች ሲፈጠሩ ደግሞ ወሳኝ እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው ብሏል፡፡
ህብረቱ የአለም ጤና ድርጅት በኮንጎ ለሚደርጋቸው የሰብአዊ እርዳታዎች የሚያደርገውን ድጋፍ በጊዜያዊነት ማቆሙንና ይህም ድርጅቱ ሌላ ቦታ በሚያደርገው ስራ ላይ ተጽእኖ እንደማይኖረው ገልጿል፡፡
ሮይተርስ የአለም ጤና ድርጅት ኃላፊዎችን ማናገሩን ምላሽ አለማግኘቱን ተናግሯል፡፡
የህብረቱ ድጋፍን ማቆሙ በአለም ጤና ድርጅትና በዋና ዳሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ በተፈጠረው ችግር ላይ እርምጃ እንዲወስዱና ድጋሚ እንዳይከሰት አንዲሰሩ ጫና አሳድሯል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ኢቦላን ለመከላከል ወደ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ልኳቸው የነበሩ ሰራተኞቹ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል መሳተፋቸው መረጋገጡን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) በዴሞክራቲክ ኮንጎ ለሥራ የተሰማሩ ባለሙያዎች በአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች በመሳተፋቸው ለተጎጅዎች አዝኛለሁ ብለውም ነበር፡፡ዶክተር ቴድሮስ ሴቶችን በመድፈር ወንጀል የተሳተፉ ሁሉ ተጠያቂ ማድረግ የድርጅቱ የመጀመሪያ ስራ ይሆናል ሲሉ ነበር፡፡