ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ አየርመንገድ 49 በመቶ ድርሻ ይዞ ኤየር ኮንጎ በዲአርሲ ሊቋቋም ነው
አዲሱ አየርመንገድ የሚቋቋመው መስከረም የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ ነው
የኢትዮጵያ አየርመንገድ ቢያንስ 7 አውሮፕላን በመያዝ በጥምር ኢንቨስትመንቱ እንደሚሳተፍ ተገልጿል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (ዲአርሲ) ጋር በመተባበር በሀገሪቱ ኤየር ኮንጎ የተባለ አየርመንገድ ሊያቋቁም መሆኑን የዲአርሲ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
አየር ኮንጎ፣ በኢትዮጵያ አየርመንገድና በዲአርሲ መንግስት በጥምረት የሚቋቋመው ሲሆን ቢያንስ 7 አውሮፕላኖችን ከኢትዮጵያ አየርመንገድ እንደሚያገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኢንቨስትመንቱ የሚገባው በኢትዮጵያ አየርመንገድና በዲአርሲ በኩል ባለ አካል በፈረንቸጆቹ መስከረም 2021 መካከል የመግባቢያ ሰነድ መፈረማቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
በኢንቨስትመንቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ 49 በመቶ ድርሻ የሚኖረው ሲሆን 51 በመቶ ደግ የኮንጎ መንግስት ድርሻ ይዞ እንደሚቋቋም ዥንዋ ዘግቧል፡፡
ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ጋር ለተደረገው ትብብር ምስጋና ይግባውና በዲአርሲ በመጭዎቹ ቀናት አዲስ አየርመንገድ “ሊወለድ ነው” ሲል ሚኒስቴሩ በትዊተር ገጹ አስፍሯል፡፡
ኮንዶ ኤርዋይስ በዲአርሲ የሚገኝ የመንግስት አየርመንገድ ሲሆን በፈረንጆቹ 2015 በ90 ሚሊዮን ዶላር ነበር የተመሰረተው፡፡