ሰሜን ኮሪያ የማተራመስ ተግባሯ እንድትታቀብ የአውሮፓ ህብረት አሳሰበ
የአውሮፓ ህብረት “የፒዮንግያንግ ድረጊት አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሰላምና ደህንነትን የሚያዳክም ነው” ብሏል
ሰሜን ኮሪያ፤ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን እንድታከብርም ህብረቱ ሳስቧል አሳስበዋል
ሰሜን ኮሪያ የማተራመስ ተግባሯን አቁማ ከዋና አጋሮች ጋር የሚደረገውን ውይይት መቀጠል አለባት ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት ጆሴፕ ቦሬል አሳሰቡ።
ጆሴፕ ቦሬል ይህን ያሉት ጃፓን፣ ቻይና እና ኮሪያ ሪፐብሊክ በሚሰተፉበትና የኢንዶ-ፓስፊክ ቀጠና የደህንነት ጉዳዮች ላይ እየመከረ ባለው የደቡብ ምስራቅ እስያ መንግስታት ማህበር (ASEAN) የካምቦዲያው ጉባኤ ላይ ነው።
ሰሜን ኮሪያ ተደጋጋሚ የባለስቲክ ሚሳዔሎችን በማስወንጨፍ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን የሚጥሱ ድርጊቶች እየፈጸመች መሆኗን ያነሱት ቦሬል፤ “የፒዮንግያንግ ድረጊት አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሰላምና ደህንነትን የሚያዳክም ነው” ሲሉም አሳስበዋል።
ሰሜን ኮሪያ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ምስራቅ የባህር ክልሏ አከባቢ የምታስወነጭፋቸው የባላስቲክ ሚሳዔሎችን በኮሪያ ልሳነ ምድር ትልቅ ግጭት እንዳይፈጥሩ ተሰግቷል።
ሚሳዔሎቹ ከምድር ከ25 እስከ 90 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ከ110 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ያክል ርቀት እንደሚበሩም ይገለጻል።
ከዚህም በተጨመሪ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ማንኛውም ወታደራዊ ግጭት ዝግጁ መሆኗን በልበሙሉነት መናገራቸው በቀጠናው አዲስ ነገር እንዳይፈጠር የሚል የበርካቶች ስጋት ሆኗል።
የሞስኮ አጋር የሆነችው ፒዮንግያንግ የሚመሩት ኪም ጆንግ ኡን፤ ከሁለት ወራት በፊት የሰሜን ኮሪያ ጦር ሃይሎች ምስረታ ቀንን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር ፤ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካም ሆነ አጋሮቿ የሚቃጡባት አደጋዎች ካሉ የመጥፋት አደጋ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ በቅረቡ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።
ከእኛ ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት የሚፈልግን ማንኛውንም ሀገር "እናጠፋለን" ሲሉ መዛታቸው የሚታወስ ነው።
በዚህም የሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳዔል ማስወንጨፍ ድርጊት፤ በደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና አሜሪካ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረ ሀገራቱ በተለያዩ ጊዜያት መግለጻቸው የሚታወስ ነው።