ፈረንሳይ ከ40 አመት በፊት የመጀመሪያውን የአውሮፓ ዋንጫ ያነሳችው ስፔንን አሸንፋ እንደነበር ይታወሳል
የአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ የአውሮፓ ሃያላኑ ስፔን እና ፈረንሳይን ያገናኝ ሲሆን፤ ጨዋታውም በስፔን የበላይነት ተጠናቋል።
በጨዋታው ላይ የስፔንን የማሸነፊያ ጎሎች የ16 አመቱ ላሚን ያማል እና ኦልሞ አስቆጥረዋል።
ፈረንሳይን ከመሸነፍ ያልታደገችውን ጎል ኮሎ ሙኣኒ ከኪሊያን ምባፔ የተሸገረለትን ኳስ ከመረብ አሳርፏል።
በጨዋታው ላይ የ16 አመቱ ላሚን ያማል በአውሮፓ ዋንጫ ታክ በትንሽ እድሜ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያ ተጫዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ጽፏል።
በጀርመኑ የአውሮፓ ዋንጫ እስካሁን 11 ጎሎችን ያስቆጠረችው ስፔን 102 የግብ እድሎችን በመፍጠርም ቀዳሚ ናት።
ለጎል አይናፋር ሆኗል የተባለው የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ግን 5 ጎል ብቻን ነው ያስቆጠረው፤ ከነዚህ ጎሎች ውስጥም ሁለቱ በፍጹም ቅጣት ምት የተገኙ ሲሆን አንደኛዋ የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች በራሱ ግብ ላይ ያስቆጠራት ናት።
ባለፉት ሁለት የአለም ዋንጫ ፍጻሜዎች ደርሳ በ2018 ያሸነፈችው፤ በ2022 ደግሞ በአርጀንቲና በመለያ ምት የተሸነፈችው ፈረንሳይ በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ እያሳየችው ያለው ብቃት አሰልጣኝ ዴሻምፕ እና የቡድኑን አባላት እያስተቻቸው ነው።
ፈረንሳይ ከ40 አመት በፊት የመጀመሪያውን የአውሮፓ ዋንጫ ስታነሳ ኮከብ እንደነበረው ሚሼል ፕላቲኒ ጎል የሚያሳድድ ተጫዋች አላገኘችም።
ከኦስትሪያ ጋር በነበረው ጨዋታ አፍንጫውን የተሰበረው ምባፔም የፊት ጭምብል አድርጎ እየተጫወተ ቢሆንም በጀርመን የተጠበቀውን ያህል አልሆነም።
አማካዩ ዩሱፍ ፎፋና ግን “ግማሽ ፍጻሜ እኮ ደርሰባል፤ በምባፔም ሆነ አንቶኒ ግሪዝማን ላይ የሚነሱ ትችቶች ስሜት አይሰጡኝም” በሚል ትችቱ አይገባንም ብሏል።
አማካዩን ፔድሪ በጉዳት ተከላካዮቹ ዳኒ ካርቫሃል እና ሮቢን ለ ኖርማንድ በሩብ ፍጻሜው ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ፈረንሳይን የሚገጥመው ቡድን አባል አይደሉም።
ፈረንሳይ ከ40 አመት በፊት የመጀመሪያውን የአውሮፓ ዋንጫ በፓርክ ደ ፕሪንስ ያነሳችው ስፔንን አሸንፋ እንደነበር ይታወሳል።
የኪሊያን ምባፔ ሀገር ሁለተኛውን የአውሮፓ ዋንጫ ከ24 አመት በፊት በ2000 ማንሳቷንም መረጃዎች ያወሳሉ።