የጣሊያን የባሕር ላይ ጠባቂዎች ከሊቢያ የተነሱ ከ500 በላይ ስደተኞችን ህይወት ታደጉ
ስደተኞቹ በአደገኛ ሁኔታ በአሳ ማጥመጃ ጀልባ ላይ ሆነው ጉዞ ሲያደርጉ ነበር
ስደተኞቹ ላምፕዱሳ ደሴት ላይ ወደ ሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ተወሰደዋል
የጣሊያን የባሕር ላይ ጠባቂዎች መነሻቸውን ከሊቢያ ያደረጉ እና ወደ አውሮፓ በማቅናት ላይ የነበሩ 539 ስደተኞችን ህይወት መታደጋቸው ተሰምቷል።
ስደተኞቹ በአደገኛ ሁኔታ በአሳ ማጥመጃ ጀልባ ላይ ሆነው ጉዞ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፤ በባሕር ላይ ጠባቂዎቹ በተደረገላቸው ድጋፍ ላምፐዱሳ ደሴት ላይ እንዲያርፉ ተደርጓል።
የባሕር ላይ ጠባቂዎች ስተደኞችን በትናትናው እለት የታደጉ ሲሆን፤ ከስደተኞች ውስጥም ህጻናት እና ሴቶች እንደሚገኙበትም የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል
ስደተኞቹ በሁለት የባሕር ላይ ጠባቂዎች ጀልባ እና ከጣሊያን የገንዘብ ወንጀሎች ፖሊሰ ጀልባዎች ስደተኞችን ወደ ላምፕዱሳ ደሴት ማጓጓዛቸውም ተሰምቷል።
ላምፕዱሳ ደሴት ከንቲባ ቶቶ ማርቴሎ፤ በትናትናው እለት ወደ ደሴቷ የተወሰዱ ስደተኞችን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ወደ ደሴቷ ሲገባ የመጀመሪያው ነው ብለዋል።
ላምፕዱሳ ደሴት ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሸጋገር ለሚያደርጉት ጉዞ ከዋነኛዎቹ መዳረሻዎች ውስጥ አንዷ ስትሆን፤ ባሳለፍነው ግንቦት ወር ከ1 ሺህ በላይ ስደተኞች ደሴቷ ላይ ደርሰው ነበር።
በደሴቷ ላይ ቁጥራቸው ከ300 ያነሱ ስደተኞችን ብቻ ማስተናገድ የሚችል መጠለያ ጣቢያ ቢኖርም፤ መጠለያው አሁን ላይ ከማስተናገድ አቅሙ በሶስጥ እጥፍ የሚበልጥ ስደተኞችን ለመያዝ ተገዷ።