እስራኤል የፍልስጤም እንደሀገር መቋቋም የደህንነት ስጋት እንደሚፈጥርባለች ትገልጻለች
ፍልስጤም ዓለም የሀገርነት እውቅና እንዲሰጣት ስትጠይቅ ቆይታለች።
ከወራት በፊት ዌስትባንክን የሚያስተዳድረው የፍልስጤም ባለስልጣን ወይም ፓሊስቴኒያን ኦቶሪቲ ለፍለስጤም ሙሉ የተመድ አባልነት እውቅና እንዲሰጥ ለተመድ አመልክቶ ነበር።
ነገርግን ጉዳዩ ለሚመለከተው የተመድ ኮሚቴ ከቀረበ በኋላ አባል ሀገራት እውቅና ለመስጠት ሳይስማሙ ቀርተዋል።
ተመድ እንደ ድርጅት የአባልነት እውቅና ባይሰጣትም ሀገራት እውቅና እየሰጧት ይገኛሉ። በቅርቡ ሶስት የአውሮፓ ሀገራት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ሰጥተዋል። በአውሮፓ ካሉት 27 ሀገራት ውስጥ እስካአሁን 12 ሀገራት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ሰጥተዋታል።
እውቅና የሰጡት 12ቱ የአውሮፓ ሀገራት የሚከተሉት ናቸው።
-ስዊድን
-ሳይፕረስ
-ሀንጋሪ
-ቼክ ሪፐብሊክ
-ፖላንድ
-ስሎቫኪያ
-ሮማኒያ
-ቡልጋሪያ
-ስፔን
-ኖርዌይ
-አየርላንድ
-ስሎቬኒያ
እስራኤል ለፍልስጤም የሚሰጥን እውቅና በጽኑ ትቃወማለች።
እስራኤል እንደምትለው ከሆነ ሀገራት ለፍልስጤም የሚሰጡት እውቅና ለሽብርተኛ ድርጅት የልብልብ የሚሰጥ ነው የሚል መከራከሪያም ታቀርባለች።
እስራኤል የፍልስጤም እንደሀገር መቋቋም የደህንነት ስጋት እንደሚፈጥርባለች ትገልጻለች።
የአረብ ሀገራት እና ተመድ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው ከእስራኤል ጎን የፍልስጤም ሀገር መቋቋምን የሚደግፈው የ "ቱ ስቴት ሶሉሽን" ሲተገበር ነው የሚል አቋም ያንጸባርቃሉ።