ሶሎቬኒያ ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና የሰጠችው የሀገሪቱ ፓርላማ ባለፈው ማክሰኞ እለት የመንግስትን ውሳኔው ካጸደቀው በኋላ ነው ተብሏል
ስሎቬኒያ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ሰጠች።
ሶሎቬኒያ ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና የሰጠችው የሀገሪቱ ፓርላማ ባለፈው ማክሰኞ እለት የመንግስትን ውሳኔው ካጸደቀው በኋላ ነው ተብሏል።
የስሎቬኒያ መንግስት ለፍልስጤም የነጻ እና ሉአላዊ ሀገርነት እውቅና የሰጠው፣ ስፔን፣ አየርላንድ እና ኖርዌይ እስራኤል በጋዛ እያካሄደች ያለውን ጦርነት እንድታቆሞ ይረዳል በሚል እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ ነው።
"በዛሬው እለት ለፍልስጤም የሉአላዊ እና የነጻ ሀገርነት እውቅና መስጠታችን በዌስትባንክ እና በጋዛ ላለው የፍልስጤም ህዝብ ተስፋ የሚሰጥ ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ጎሎብ በኤክስ ገጻቸው ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ ድምጽ ለመስጠት በትናንትናው እለት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ሲሆን የውጭ ጉዳይ የሚመለከተው የፓርላማ ቡድን መንግስት ያቀረበውን ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
ቀደም ሲል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ የሆነው ቀኝ ዘመሙ ስሎቬኒያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ(ኤስዲኤስ) የእውቅና መስጠቱ ጉዳይ ውይይት እንዲደደረግበት ጥያቄ በማቅረቡ ድምጽ የመስጠቱ ሂደት ቢያንስ በአንድ ወር እንዲዘገይ ማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል።
በሀገሪቱ ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ ኤስዲኤስ "ሽብርተኛ ድርጅት የሆነውን ሀማስን" ስለሚያበረታታ ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት ለመስጠት አሁን ጊዜው አይደለም የሚል መከራከሪያ አቅርቦ ነበር።
90 አባለት ባሉት የስሎቬኒያ ገዥ ፓርቲ ምርጫው እንዲካሄድ በማድረግ የመንግስት እውቅና የመስጠት ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
እስራኤል የፍልስጤምን ነጻ ሀገርነት አትቀበልም፣ እውቅና የሚሰጧትን ሀገራትም በጽኑ ትቃወማለች።
የአረብ ሀገራት እና ተመድ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው ከእስራኤል ጎን የፍልስጤም ሀገር መቋቋምን የሚደግፈው የ "ቱ ስቴት ሶሉሽን" ሲተገበር ነው ይላሉ።