አማርኛን የሚያስተምሩ የአውሮፓ ዩንቨርሲቲዎች
አማርኛ በሰሜቲክ ቋንቋዎች ምድብ ውስጥ ካሉ ቋንቋዎች ውስጥ በተነጋሪዎች ብዛት ከአረብኛ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል
ቋንቋው በአውሮፓ ብቻ በስምንት የአውሮፓ ዩንቨርሲቲዎች ይጠናል ተብሏል
አማርኛን የሚያስተምሩ የአውሮፓ ዩንቨርሲቲዎች
የኢትዮጵያው አማርኛ ቋንቋ በአውሮፓ ባሉ ዩንቨርሲቲዎች ማስተማር ከተጀመረ አንድ ክፍለ ዘመን አልፎታል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ የጀርመኑ ሐምቡርግ ዩንቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ ዙሪያ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ እንደገለጸው በሴሜቲክ ቋንቋዎች ምድብ ስር ካሉ ቋንቋዎች ውስጥ አማርኛ በተናጋሪ ብዛት ከአረብኛ በመቀጠል ሁለተኛው ነው፡፡
ቋንቋው ከሚሰጥባቸው ሀገራት መካከል ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ሩሲያ እና ሌሎችም ሀገራት ዋነኞቹ ናቸው፡፡
የጀርመኖቹ በርሊን እና ሐምቡርግ ዩንቨርሲቲዎች አማርኛ ቋንቋን ከሚያስተምሩት መካከል ሲጠቀሱ ኔፕልስ፣ ፓሪስ፣ ዋርሶው፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ እና ለንደን ዩንቨርሲቲዎችም በማስተማር ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
የዓለማችን ቁጥር ሁለት ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና አማርኛን ከሚያስተምሩት ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ሩሲያ ደግሞ ከዩንቨርሲቲ ባለፈ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በማስተማር ላይ ትገኛለች፡፡