ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን አስመረቀች
የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲሰቱ በአማርኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎቹን አስመርቋል
አማርኛ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ነው
ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በትናትናው እለት አስመርቃለች።
በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) በትናናው አልተ ተማሪዎቹን ያመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎቹ መካከልም በአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎቹ ይገኙበታል።
በቻይና የኢትዮጵያ ኤማባሲ ተወካዮች ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ምርቃት ላይ መሳተፋቸውንም ኤምባሲው አስታውቋል።
“በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU በቻይና ውስጥ ብቸኛው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል የሚሰጥ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ ትናንት ከተመረቁት መካከል የመጀመሪያው ዙር የአማርኛ ተማሪዎች ይገኙበታልብሏል ኤምባሲው ባወጣው መረጃ።
ኤምባሲው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠቱን አመስግኖ፤ “ይህ የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያጠናክራል” ብሏል።
የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ መማሪያ መጽሃፍትን ባሳለፍነው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ማስተማር መጀመሩን ይፋ ያደረገው በፈረንጆቹ 2022 ላይ ነበር።
ዩኒቨርስቲው ከቀዳሚ የቻይና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ ነው።
ሃይዲያን በተሰኘው የቤጂንግ አካባቢ የሚገኝም ሲሆን ምስራቅና ምዕራብ ብለው የተከፈሉ ሁለት ካምፓሶች አሉት።
ተጠሪነቱ በቀጥታ ለሃገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር የሆነው ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰዓት አማርኛን ጨምሮ በ101 የውጭ ሃገራት ቋንቋዎች በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ያስተምራል።