ዛሬ መስከረም 4 2017 ባንኮች 1 ዶላርን በስንት ብር እየመነዘሩ ነው?
ባንኮች አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በሃዋላ ለሚላክ የውጭ ምንዛሬ ከመደበኛው የተሻለ ዋጋ አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመደበኛ የምንዛሬ ተመን 1 ዶላር በ108.0728 ብር ገዝቶ በ119.9068 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያውያን በልዩ የዘመን ቀመራቸው የተቀበሉትን አዲስ አመት 2017 በማስመልከት ባንኮች ከውጭ ለሚላክ ገንዘብ የሚያቀርቡት የምንዛሬ ተመን ላይ ማሻሻያ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።
ዲያስፖራው በህገወጡ (ጥቁር ገበያ) ከመላክ ይልቅ ህጋዊውን መንገድ እንዲመርጥ የሚያበረታታ ተመንም እያወጡ ሲሆን፤ ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የመስከረም 4 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዓመትን ምክንያ በማድረግ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የሚላክን ገንዘብ ከባንኩ ለሚቀበሉ ደንበኞቹ ተጨማሪ የ6.82 በመቶ የበዓል ስጦታ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ባንኩ ዛሬ መስከረም 4 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ባለፉት ቀናት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል፤ 1 ዶላርን በ108.0728 ብር እየገዛ በ119.9068 ብር እየሸጠ ይገኛል።
እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚላክን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር እንደሚመነዝር ያስታወቀው ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል።
በዚህም ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ107.8729 ብር እየገዛ በ120.8176 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ዳሸን ባንክም በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የምንዛሬ ዋጋ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን ከመደበኛው የምንዛሬ ዋጋ ላይ እስከ 16 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ባንኩ በመደበኛ የምንዛሬ ዋጋው ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ108.0703 ብር እየገዛ በ121.5791ብር እየሸጠ መሆኑን ነው ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ ያደረገው።
አቢሲኒያ ባንክም በዓልን ምክንያት በማድረግ ከውጪ በሃዋላ የተላከ አንድ የአሜሪካ ዶላርን ከእለታዊ ተመን በተጨማሪ 16% ጉርሻ እንደሚሰጥ እና በዚህም 1 ዶላርን እስከ 125 ብር እንደሚመነዝር ማስታወቁ ይታወሳል።
ባንኩ የዛሬ የመስከረም 4 2017 መደበኛ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ 1 የአሜሪካ ዶላር በ108.0729 ብር እየገዛ በ121.0416 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የጠቆመው።