ጀርመን 250 ሺህ ስራ ፈላጊ ኬንያውያንን ለመቀበል ስምምነት ፈጸመች
ስምምነቱን የጀርመኑ ፕሬዝደንት ኦላፍ ሽሎዝ እና የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በበርሊን ተፈራርመዋል
ኬንያ ለስራ አጥ ወጣቶቿ ስራ ለመስጠት የተቸገረች ሲሆን ጀርመን በአንጻሩ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት አጋጥሟታል
ጀርመን 250 ሺህ ስራ ፈላጊ ኬንያውያንን ለመቀበል ስምምነት ፈጸመች።
ጀርመን ሙሉ እና ከፊል ስልጠና የወሰዱ 250ሺ ኬንያውያን ተቀብላ ስራ ለመቅጠር ከኬንያ መንግስት ጋር መስማማቷን ቢቢሲ ዘግቧል።
ኬንያ ለስራ አጥ ወጣቶቿ ስራ ለመስጠት የተቸገረች ሲሆን ጀርመን በአንጻሩ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት አጋጥሟታል። እስካሁን እንደማስጀመሪያ አምስት ኬንያውያን የአውቶቢስ ሹፌሮች በሰሜን ጀርመን ገብተዋል።
ጀርመን ስደትን ለመቀነስ የስደተኝነት ስምምነቶችን እንደዋና መሳሪያ ትጠቀማለች። ይህ ስምምነት ያለህጋዊ ፈቃድ በጀርመን የሚኖሩ ኬንያውያን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሂደቱንም ያቃልላል ተብሏል።
በጀርመን የቀኝ አክራሪ የሆነው 'አልተርኔት ፎር ጀርመኒ' ፓርቲ ብቅ ማለቱን ተከትሎ የስደት ጉዳይ ትልቅ ጉዳይ ነው።
በበርሊን ያሉ መንግስታት በአንጻራዊት ብዙ ቀጥር ያላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች እንዲኖሩ ሲፈቅዱ ቆይተዋል።
ጀርመን ጦርነት ሸሽተው በአብዛኛው ከሶሪያ የመጡ አንድ ሚሊዮን ገደማ ስደተኞችን እንዲሁም ሩሲያ በ2022 በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ከከፈተች በኋላ ደግሞ 1.2 ሚሊዮን ዩክሬናውያንን ተቀብላ እያስተናገደች ነው።
የስራ ስምምነቱን የጀርመኑ ፕሬዝደንት ኦላፍ ሽሎዝ እና የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በበርሊን ተፈራርመዋል። ጀርመን ኬንያውያን ባለፈው ግዙፍ ኢኮኖሚ ስራ እንዲያገኙ የተወሰኑትን የስደተኝነት ህጎቿን አቃላለች።
የበርሊን ባለስልጣናት በጀርመን የስራ ፈቃድ ላላቸው ኬንያውያን ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠትም ተስማምታለች።
ከዚህ በተጨማሪም ኬንያውያን ለትምህርት እና ለሙያ ስልጠና የረጅም ጊዜ ቪዛ ያገኛሉ ተብሏል።