በአየር ንብረት ለውጥ በርካታ ህጻናት የተፈናቀሉባቸው ሀገራት
ከ43 ሚሊየን በላይ ህጻናት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ተፈናቅለዋል
ጎርፍ እና የድርቅ አደጋዎች ሚሊየኖችን ከቀያቸው አፈናቅለዋል
ዩኒሴፍ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በርካታ ህጻናት የተፈናቀሉባቸውን ሀገራት ይፋ አድርጓል።
በመላው አለም ከ2016 እስከ 2021 ባሉት ስድስት አመታት 43 ነጥብ 1 ሚሊየን ህጻናት ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።
ጎርፍ፣ ድርቅ እና የሰደድ እሳት አደጋዎች ህጻናትን ከቀያቸው በማፈናቀሉ ረገድ ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።
በዩኒሴፍ ሪፖርት መሰረት በተጠቀሰው አመት ውስጥ በርካት ህጻናት የተፈናቀሉባት ፊሊፒንስ ናት።
በህንድ እና ቻይና ከ6 ሚሊየን በላይ ህጻናት በጎርፍ እና ማዕበል ምክንያት የተፈናቀሉ ሲሆን፥ በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የተከሰቱ የድርቅ አደጋዎች ሚሊየኖችን አፈናቅሏል።
ዩኒሴፍ በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በርካታ ህጻናት የተፈናቀሉባቸው ሀገራት ናቸው ብሎ የዘረዘራቸውን ይመልከቱ፦