ተመራማሪዎች ኒያንደርታል የተሰኘውን የሰው ዝርያ የፊት ገጽታ ይፋ አደረጉ
ከ75 ሺህ ዓመታ በፊት አንድ የኒያንደርታል ዝርያ ፊት ምን እንደሚመስል በቴክኖሎጂ የተደግፈ የፊት ገጽታ ተሰርቷል
ኒያንደርታል የተሰኘው የሰው ዝርያ በአውሮፓ እና እስያ ላለው የሰው ልጅ ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል
ተመራማሪዎች ኒያንደርታል የተሰኘውን የሰው ዝርያ የፊት ገጽታ ይፋ አደረጉ፡፡
ከ75 ሺህ ዓመት በፊት በአውሮፓ እና እስያ ይኖራል ተብሎ የሚገመተው የሰው ዝርያ ኒያንደርታል የሚሰኝ ሲሆን አሁን ላለው የሰው ዝርያ ዋነኛ ምንጭ እንደሆነ የከርሰ ምድር እና ቅሪተ አካል ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡
በካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ የቅርቲ አካል ተመራማሪዎች 3ዲ የተሰኘውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከ75 ሺህ ዓመታት በፊት በህይወት የምትኖር የኒያንደርታል የሰው ዝርያ የፊት ቅርጽ ምን እንደሚመስል ይፋ አድርገዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ይህች በ40 ዓመቷ ህይወቷ እንዳለፈች የምትገመተው የኒያንደርታል የሰው ዝርያ የፊቷን ቅርጽ ለመሳል በቅሪተ አካል ቁፋሮው ወቅት የተገኙ የተወሰኑ የሰውነት ክፍሏ አጥንትን እንደመነሻ በመውሰድ መዘጋጀቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከ92 ዓመት በኋላ የሰው ልጅ ስራዎች ሙሉ ለሙሉ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ይተካሉ ተባለ
በቅሪተ አካል ቁፋሮ ወቅት የተገኘው የተወሰነ የራስ ቅልን መነሻ በማድረግም ተቀራራቢ ፊቷን ኔዘርላንዳዊው የእንስሳት ቅርጽ ስዕል ባለሙያዎቹ አንድሬ እና አልፎንስ ኬኒስ ሰርተውታልም ተብሏል፡፡
የፊት ቅርጿ በ3ዲ ቴክኖሎጂ የተሰራላት የኒያንደርታል የሰው ዝርያ በኢራቋ ኩርዲስታን ግዛት ልዩ ስፍራው ሻኒዳር በተሰኘ ስፍራ በ1950ዎቹ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው፡፡
ከ40 ሺህ ዓመት በፊት በምድር ላይ ይኖር ነበር የተባለው ይህ የኒያንደርታል የሰው ልጅ ዝርያ ቅሪተ አካሎች በአውሮፓ እና እስያ ተገኝተዋል፡፡
ይህ የሰው ልጆች ዝርያ ኒያደርታል የሚለውን ስያሜ ያገኘው በጀርመን ኒያንደርታል ዋሻ ከሚባለው ስፍራ እና ይህም ዝርያ በዚህ ስፍራ ይኖር እንደነበር የተገኙ ቅሪተ አካል ማስረጃዎች አረጋግጠዋልም ተብሏል፡፡