የእስራኤል ተመራማሪዎች ያለ ወንድ ዘር የሰው ልጅ ጽንስ መፍጠር መቻላቸውን ገለጹ
ተመራማሪዎቹ ያለ ወንድ ዘር፣ እንቁላል እና ማህጸን በቤተ ሙከራ የሰው ልጅ ጽንስ ፈጥረናል ብለዋል
ሌሎች ተመራማሪዎች ግን ድርጊቱን ኮንነው የተቹ ሲሆን ተፈጥሯዊ የጽንስ አፈጣጠርን ማሻሻል እንደማይቻል ገልጸዋል
የእስራኤል ተመራማሪዎች ያለ ወንድ ዘር የሰው ልጅ ጽንስ መፍጠር መቻላቸውን ገለጹ፡፡
የእስራኤል ተመራማሪዎች የሰው ልጅ ስፐርም ወይም የወንድ ዘር ፣ የሴት እንቁላል እና ማህጸንን ሳይጠቀሙ የሰው ልጅ ጽንስ መፍጠር መቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሮይተርስ ተመራማሪዎቹን ዋቢ አድርጎ በሰራው ዘገባ ስቲም ህዋስን በመጠቀም በቤተ ሙከራ በመታገዝ የሰው ልጅ ጽንስ መፍጠራቸው ተገልጿል፡፡
የተመራማሪዎቹ ግኝት በሰው ልጅ ጽንስ ዙሪያ አዲስ ፈጠራ ነው የተባለ ሲሆን ክስተቱ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
የእስራኤሉ ዌዝማን ሳይንስ ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት እነዚህ ሳይንቲስቶች በቤተ ሙከራ ውስጥ በ14 ቀን ውስጥ ጽንስን ፈጥረናል ብለዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በአሜሪካ ቦስተን በተካሄደው ዓለም አቀፍ የስቲም ህዋስ ጥናት መድረክ ላይ እስካሁን የደረሱበትም የምርምር ደረጃ አቅርበዋል ተብሏል፡፡
“ስካይ ሶኒክ” - የእስራኤል የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ጥቃት ጋሻ
ተመራማሪዎቹ ካለሰው ልጅ ስፐርም እና አንንቁላል የሰው ልጅ ጽንስ መፍጠር መቻላቸው አዲስ ግኝት ነው የተባለ ሲሆን ተጨማሪ ምርምሮች እንደሚያስፈልጉ ተገልጿል፡፡
እንደተመራማሪዎቹ ገለጻ ጽንስ መፍጠር የተቻለው ከሰው ልጅ ቆዳ ላይ የተወሰዱ ህዋሳትን በቤተ ሙከራ እንዲበለጽጉ ከተደረጉ ሌሎች ህዋስ ጋር በማዋሃድ ሲሆን ከዚያም ወደ ተለያዩ ህዋስ እንዲለወጡ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡
የተመራማሪዎቹ ቀጣይ እቅድም በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ እና አስተማማኝ ምርምሮችን ማድረግ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ሌሎች ተመራማሪዎች ግን ትችቶችን ሰንዝረዋል፡፡
በካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ የስቲም ሴል ተመራማሪ የሆኑት ማገዳሊና ዘርኒካ በተያዘው ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድስት ምርምሮች መካሄዳቸውን ገልጸው የእስራኤል ተመራማሪዎች የሰሩት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ምርምር በሰው ልጅ ጽንስ አፈጣጠር ላይ ተጨማሪ ምርምሮች እንዲደረጉ የሚያበረታታ መሆኑን የተናገሩት ተመራማሪዎቹ የሰው ልጅ ጽንስ አፈጣጠርን ከተፈጥሯዊው የተሻለ አድርገን መስራት የሚቻል አይመስለኝም ብለዋል፡፡