ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በአውሮፖ ከማስታወቂያ ነጻ የሆነ አገልግሎት ሊሰጥ ይችላሉ ተባለ
ሜታ በሚቀጥሉት ወራት ከአውሮፖ ህብረት የመረጃ ሚስጥራዊነት ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም የክፍያ አገልግሎት አንደሚሰጥ ሲገለጽ ቆይቷል
ሜታ እነዚህን ማህበራዊ ሚዲያዎች ከነማስታወቂያቸው ወይም ያለማስታወቂያ በክፍያ የሚጠቀሙበትን ምርጫ ለደንበኞች ሰጥቷል
በአውሮፖ ያሉ የፌስቡክ እና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ከማስታወቂያ ነጻ የሆነ አገልግሎት ሊያገኙ እንደሚችሉ የአሜሪካው ዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ ዘግቧል።
የፌስቡክ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ በሚቀጥሉት ወራት ከአውሮፖ ህብረት የመረጃ ሚስጥራዊነት ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም የክፍያ አገልግሎት አንደሚሰጥ ሲገለጽ ቆይቷል።
እንደ ጋዜጣው ከሆነ ሜታ እነዚህን ማህበራዊ ሚዲያዎች ከነማስታወቂያቸው ወይም ያለማስታወቂያ በክፍያ የሚጠቀሙበትን ምርጫ ለደንበኞች ሰጥቷል።
ኩባንያው ባወጣው መግለጫ "ሜታ በማስታወቂያ የተደገፈ ነጻ አገልግሎት መሰጠት ያለውን ዋጋ ይረዳል" ብሏል።
"ነገርግን እየወጡ ካሉ የቀጥጥር መስፈርቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ለመቀጠል የተለያዩ አማራጮች መፈለጋችንን ቀጥለናል። ሌላ በዚህ ወቅት የምናጋራው የለም።" ብሏልለ ኩባንያው።
የአውሮፖ ህብረት ፍርድ ቤት ባለፈው ሐምሌ ወር ሜታ ማስታወቂያዎችን ለተጠቃሚዎች ከመልቀቁ በፊት ፍቃድ ማግኘት አለበት ብሎ ነበር። ነገርግን ኩባንያው የሚያገኛቸውን ማስታወቂያዎች እንደተጠቃሚዎች ፍላጎት በመልቀቅ የሚያገኘውን ገበያ የሚያሳጣ መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ያለውን በበጎ አልተቀበለውም።
በዚህ የሜታ እቅድ ላይ የህብረቱ ተቆጣጣሪዎች መፍቀዳቸው ወይም አለመፍቀዳቸው አልታወቀም።ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለአውሮፖ ተጠቃሚዎች ከማስታወቂያ ነጻ የሆነ አገልግሎት ሊሰጥ ይችላሉ ተባለ
ፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለአውሮፖ ተጠቃሚዎች ከማስታወቂያ ነጻ የሆነ አገልግሎት ሊሰጥ ይችላሉ ተባለ