ፌስቡክ በአሜሪካ በአሸባሪነት የተፈረጀውን የታሊባንን መልእክት ማገዱን እንደሚቀጥል ገለጸ
ፌስቡክ የታሊባን ይዘት ያላቸውን መልእክት እንዳይሰራጩ ያደረጋል ብሏል
አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ታሊባን ከ20 አመታት በኋላ ቤተመንግስት ገብቷል
የፌስቡክ ኩባንያ ከታሊባን ጋር የተያያዙ መልክቶችን እንደሚያግድ እና ታሊባንንም አሸባሪ ቡድን አድርጎ እንደሚመለከት አስታውቋል፡፡
ኩባንያው፤ ከታሊባን ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያጣሩ ጠንካራ ባለሙያዎች እንዳሉት ተናግሯል፡፡ ፌስቡክ፤ እስከዛሬ ድረስ ቡድኑ መልዕክቶቹን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሰራጨት ፌስቡክን እንደ አንድ መገናኛ አማራጭ ሲጠቀምበት መቆየቱ ተገልጿል፡፡
የፌስቡክ ቃል አቀባይ፤ ታሊባን በአሜሪካ ሕግ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ መፈረጁን ገልጸው ኩባንያውም ታሊባን አገልግሎቱን እንዳያገኝ እንደሚያደርግ ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡
ታሊባን ፌስቡክን እንዳይጠቀም ለማድረግ የአፍጋኒስታን ባለሙያዎች ቡድን ማዋቀሩንም ነው ኩብንያው ያስታወቀው፡፡ በባለሙያዎች በመታገዝ የታሊባን ይዘት ያላቸውን የፌስቡክ መልዕክቶቸች ወዲያውኑ ከፌስቡክ ላይ እንደሚያጠፋም ፌስቡክ ይፋ አድርጓል፡፡ ፌስቡክ ይህንን የሚያደርገው የአደገኛ ድርጅቶች ፖሊሲዎች በሚል ሲሆን ታሊባንንም በዚህ ፖሊሲ ማዕቀፍ እንደሚመለከተው ገልጿል፡፡
ፌስቡክ፤ የታሊባንን መልዕክቶች ከፌስቡክ ባለፈም ድርሻዎቹ በሆኑት ኢንስታግራምና ዋትስአፕ ጭምር እንደሚያግድ አስታውቋል፡፡
አሜሪካ ከፍጋኒስታን ወታደሮቿን ማስወጣቷን ተከትሎ ለ20 አመታት ያህል የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የነበረው ታሊባን በአጭር ቀናት ውስጥ ቤተመንግስት መግባት ችሏል፡፡
ታሊባን የአፍጋኒስታንን ዋና ከተማ ከመቆጣጠሩ ቀደም ብሎ ሀገሪቱን ሲመሩ የነበሩት አሽራፍ ጋኒ ወደ ጎረቤት ሀገር ሸሽተዋል፡፡
ታሊባንን በአሸባሪነት ፈርጀው፣ በአፍጋኒስታን ወታደር አሰማርተው የነበሩት አሜሪካና እንግሊዝን ጨምሮ ሌሎች የምእራባውያን ሀገራት ዲፕማቶቻቸውን በልዩ ዘመቻ ከአፍጋኒስታን ሲያስወጡ ታይተዋል፡፡
የታሊባንን ካቡል መግባት ተከትሎ በካቡል ከፍተኛ ትርምስ ተከትስቷል፤በአየርመንገድም ብዙ ሰዎች ወደ ውጭ ለመውጡት በውታደራዊ አውሮፕላን ላይ ሲንጠላጠሉ ነበር፡፡ ከአሜሪካ ጋር ሲሰሩ የነበሩ የአፍጋን ዜጎች ታሊባን ይበቀለናል በሚል ፍርሃት ውስጥ ናቸው፡፡