የካቡል ነዋሪዎች ስጋ ውስጥ የገቡ ሲሆን፤ አፍጋስታን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በካቡል ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር ነው ብሏል
የታሊባን ታጣቂዎች ወደ አፍጋኒስታኗ ዋና ከተማ ካቡል በሁሉም አቅጣጫ መግባታቸውን የአፍጋኒስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ።
የታሊባን ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ መግባት መጀመራቸውን ተከትሎ ሰይረኖች እየተሰሙ ሲሆን፤ አልፎ አልፎ ተኩስ እንደሚሰማ እና ሂሊኮፕተሮችም በከተማዋ ሰማይ ላይ በስፋት እተስተዋሉ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
የታሊባን ቡድን ባወጣው መግለጫ የአፍጋኒስታን ዋና ከተማ የሆነችውን ካቡልን በጉልበት የመያዝ እቅድ እንደሌለው አስታውቋል።
ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ የሽግርግር ሂደት ለመጀመር ድርድሮች እየተካሄዱ ነው ያለው ታሊባን፤ ሂደቱን የካቡል ነዋሪዎችን ሕይወት እና ንብረት ጉዳት ላይ በማይጥል መልኩ እየተካሄደ ነው ብሏል።
የታሊባን ቃል አቀባይ በትዊተር ገጽ ባስተላፈው መልእክትም፤ ሁሉም ሀይሎች ወደ ከተማዋ ለመግባት ሙከራ እንዳያደርጉ እና በሁሉም የከተማዋ መግቢያ ላይ በተጠንቀቅ እንዲቆዩ ትእዛዝ እንደተሠ አስታውቋል።
ከተማዋ የአይን እማኞች እንደሚናገሩት ከሆነ ደግሞ ተወሰኑ የታሊባን ታጣቂዎች የካቡል ከተማ ጠረፍ አካባዎች ላይ መግባ ጀምረዋል።
በሁኔታው የተደናገጡ መንግስት ሰራተኞች ቢሮዋቸውን ለቀው መውጣታቸው የተነገረ ሲሆን፤ በርካታ ሲቪሊያን የሚሆነውን ነገር በስጋት ውስጥ ሆነው እተጠባበቁ ይገኛሉም ተብሏል።
የፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋህኒ ጽህፈት ቤት ሀላፊ በትዊተር ገጻቸው ባስተላፉት መልእክት ፤ ነዋሪዎች ምንም ስጋት እንዳይገባቸው በመጥቀስ፤ አሁን በካቡል ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር ነው ብለዋል።
በአፍጋኒስታን ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ያለው የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር (ኔቶ) እና የአሜሪካ ጦር ከ20 ዓመታት በኋላ መውጣታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ይታወቃል።
ታሊባን የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ከስልጣን ካልተነሱ ሰላም እንደማይረጋገጥ ቀደም ብሎ መግለጹ ይታወሳል።
የአሜሪካ እና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከአፍጋኒስታን ለቆ መውጣት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ታሊባን የአፍጋኒስታንን በርካታ ግዛቶች መቆጣጠሩን እየገለጸ ነው።