የአሜሪካ ጦር አፍጋኒስታንን ለቆ መውጣትን ተከትሎ ታሊባን የሀገሪቱን በርካታ ግዛቶች እተቆጣጠረ ነው
ታሊባን አስረኛዋ የአፍጋኒስታን ግዛት የሆነችውን እና ከአፍጋን መዲናዋ ካቡል 150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን ጋዝኒ ከተማ መቆጣጠሩ ተገለጸ።
የግዛቱ ምክር ቤት ኃላፊ ናስር አህመድ “ታሊባን የከተማዋ ቁልፍ ቦታዎች፣ የመንግስት መስርያ ቤቶች፣ የፖሊስ ጽህፈት ቤቶች እና እስር ቤት ተቆጣጥሯል” ብለዋል።
ቀደም ሲል በሄልማን ግዛት ውስጥ የአሜሪካ የአየር ድብደባ አካባቢውን ሲመታ ታጣቂዎቹ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤትን በቁጥጥር ስር ማዋላቻንም የፈረንሳዩ የዜና ወኪል/ኤ ኤፍ ፒ/ ዘግቧል።
ሶሞኑን እየተካሄደ ያለውን ውግያ በተመለከተ በአፍጋኒስታን መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
ይሁን እንጅ የፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋህኒ መንግስት በሀገሪቱ ልዩ ኃይል አማካኝነት እንዲሁም ከአሜሪካ አየር ኃይል እና ኔቶ ኃይሎች ጋር በመተባበር መልሶ ማጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ መሆናችን ገልጸዋል።
ለዚህም የካቡል መንግስት የሀገሪቱ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ዋሊ ሞሃመድን በአዲስ ኢታማዦር ሹም ተክቷል።
የአፍጋን መዲና ካቡል አስካሁን ስጋት ላይ ባትሆንም ግን የታጣቂዎቹ ወታደራዊ እርምጃና ፍጥነት መጨረሻው የት ይሆን የሚለው ጥያቄ መፍጠሩ አልቀረም።
እስካሁን ባለው መረጃ በታጣቂዎቹ እና በመንግስት ባለው ግጭት በሺዎች የሚዎጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል።
በአፈጋኒስታን ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ያለው የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እና የአሜሪካ ጦር ከ20 ዓመታት በኋላ መውጣታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ሲገለጽ ቆይቷል።
ታሊባን የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ከስልጣን ካልተነሱ ሰላም እንደማይረጋገጥ ቀደም ብሎ መግለጹ ይታወሳል።
የአሜሪካ እና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከአፍጋኒስታን ለቆ መውጣት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ታሊባን የአፍጋኒስታንን በርካታ ግዛቶች መቆጣጠሩን እየገለጸ ነው።