“የወሊድ መከላከያ ነው” እያለ የሎሊፖፕ ከረሜላ እንጨት ክንድ ውስጥ ሲቀብር የነበረው ቬንዙዌላዊው ሀሰተኛ ዶክተር
ሎፔዝ በተጭበረበረ የህክምና የትምህርት ማስረጃ ቬንዙዌላ ውስጥ በሚገኙ 2 ጤና ጣቢያዎች ሰርቷል
ዳንኤል ሎፔዝ የወሊድ መከላከያ ነው በሚል የሸወዳቸው 25 ሴቶች ማርገዛቸው ተነግሯል
“የወሊድ መከላከያ ነው” እያለ የሎሊፖፕ ከረሜላ እንጨት ክንድ ውስጥ ሲቀብር የነበረው ቬንዙዌላዊው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር መዋሉ ተነግሯል።
ዳኒኤል ሎፔዝ የተባለው የ38 ዓመቱ ቬንዙዌላዊ በርካታ ሴቶችን የተራቀቀ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ እንደሆኑ እንዲያስቡ ማድረግ በከረሜላ እንጨት በርካቶችን እንዳታለለ ኦዲቲ ሴንተራል ዘግቧል።
ግለሰቡ በዚህም ቢያንስ ከ25 በላይ ሴቶችን የወሊድ መከላከያ ነው ያለውን የሎሊፖፕ ከረሜላ እንጨት ክንዳቸው ስር በመቅበር ገንዘብ በመቀበል ማጭበርበሩም ታውቋል።
ዳንኤል ሎፔዝ የወሊድ መከላከያ ነው በሚል የከረሜላ እንጨት ከቀበረላቸው ሴቶች ውስጥ አባዛኞቹ ላይ እርግዝና መከሰቱ እንዲያዝ ምክንያት እንደሆነም ተነግሯል።
ምንም ዓይነት የህክምና ትምህርት ያልነበረው ሎፔዝ በተጭበረበረ የህክምና ዲግሪ የትምር ማስረጃ ላ ቪክቶሪያ እና ማራካይ በተባሉ ቬንዙዌላ ውስጥ በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ሰርቷል።
በጤና ጣያዎቹ በነበረው ቆይታም በክንድ ስር የሚቀበር (ኢምፕላንት) የወሊድ መከላከያ ናቸው በማለት መጠናቸው አነስተኛ እና ቀጫጭኝ የከረሜላ እንጨቶችን በአነስተኛ ቀዶ ህክምና በክንድ ስር ሲተክል ነበር ተብሏል።
የሎፔዝ የማይታመን ማጭበርበር ለመጀመሪያ ጊዜ ግልጽ የሆነው ራፋኤል ቺሪኖስ የተባለ ትክክለኛ ዶክተር ጉዳዩን ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ይዞት ከወጣ በኋላ እንደሆነ ተነግሯል።
ይህንን ተከትሎም በተደረገ የማጣራት ስራ ዳንኤል ሎፔዝ በክንድ ስር የሚቀበር (ኢምፕላንት) የወሊድ መከላከያ ናቸው በማት ለሴቶቹ ሲተክል የነበረው ትክክለኛውን የወሊድ መከላከያ ሳይሆን የሎሊፖፕ ከረሜላ እንጨት መሆኑ ተደርሶበታል።
ጉዳዩ መራገቡን ተከትሎ አጭበርባሪው ዶከተር ዳንኤል ሎፔዝ ራሱን በመሰወር ከአካባቢው ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም፤ በኋላ ላይ ኤል ካስታኖ በተባለ ስፍራ በፖሊስ ሊያዝ ችሏል።