ዶክተሩ አብዛኛውን ጊዜ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን በቀዶ ህክምና ያስተካክላል
ህንዳዊው የፕላስቲክ የቀዶ ህክምና ዶከተር የ37 ሸህ ህጻናትን ፈገግታ በመመለሱ “ጀግና” የሚል መጠሪያ አግኝቷል።
ዶከተሩ አብዛኛውን ጊዜውን የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን በቀዶ ህክምና የማስተካከል ስራ ላይ ነው የሚያሳልፈው የተባለ ሲሆን፤ ሁሉንም የቀዶ ጥገና ህክምናዎች በነጻ ማከናወኑም ተነግሯል።
በዚህ ስራው “ጅግና” የሚል ስያሜ ያገኘው ዶክተር ሱብዶህ ኩማር፤ የልጅነት ጊዜውን በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሳለፈ ሲሆን፤ ይህም የሰዎችን ችግር እንዲረዳ እንዳደረገው ይናገራል።
“ዶክተር መሆኔ ደግሞ በርካቶችን እንደረዳ እድሎቸን ፈጥሮልኛል” የሚለው ዶከተር ሱብዶህ ኩማር፤ “በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የተሻለ ህይወትን እንዲኖሩ እንዳደርግ አስችሎኛል” ብሏል።
በዚህም የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን መርዳት እንደቻለ ያስታወቀው ዶከተሩ፤ እነዚህ ህጻናት ህክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደጀመረ ይናገራል።
ዶከተር ሱብዶህ ኩማር ከከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ጋር የተወለዱ ህጻናትን ለመርዳት የጀመረው ጥረት በኋላ ላይ በርካታ ትላልቅ ድርጅቶችን ስቦ በእነሱ ድጋፍ ስራውን መጀመሩንም አስታውቋል።
በዚህም ከከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ጋር የተወለዱ 37 ሺህ ህጻናትን የማስተካከል ቀዶ ህክምና በነጻ ማከናወን አንደቻለም ተነግሯል።
እንደ ሲዲሲ ገለጻ ህጻናት ላይ ከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር የሚያጋጥመው በእርግዝና ወቅት ከንፈራቸው አሊያም አፋቸው ላይ በሚኖር የአፈጣጠር ችግር የሚከሰት ነው።
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር በርካታ ችግሮችን የሚያሰከትል ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ እንዱ ችግሩ ያለባቸው እንደ ሌሎች ልጆች በአግባቡ ወተት የመጠጣት ችግር አንዱ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ እድሜያቸው ከፍ ሲል በሌሎች መገለል ነው።
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር በቀዶ ህክምና የሚስተካከል ሲሆን፤ ይህ ህክምና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ዋጋው የማይቀመስ ሆኖ በርካቶች ሲቸገሩ ይስተዋላል።