የእናቱን መኪና አስነስቶ ያሽከረከረው የአራት ዓመቱ ሆላንዳዊ ህጻን አነጋጋሪ ሆኗል
በህጻኑ ድርጊት የተደመሙ ሰዎች ህጻኑ እድሜው ሲደርስ ጎበዝ የመኪና ተወዳዳሪ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው
ፖሊስ፤ ህጻኑ መኪናወን በሚያሽከረክርበት ወቅት ሁለት መኪኖች እንደገጨ አረጋግጫለሁ ብሏል
የእናቱን መኪና አስነስቶ ያሽከረከረው የአራት ዓመቱ ሆላንዳዊ ህጻን አነጋጋሪ ሆኗል።
የሆላንዷ ኡትረች ከተማ ፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ፤ ፒጃማ ለብሶ የነበረው የአራት ዓመት ህጻን የእናቱን መኪና እነስቶ ሲነዳ ሁለት መኪናች ከገጨ በኋላ ባዶ እግሩ በአስፋልት ላይ ሲሄድ ታይቷል።
በዚህም ህጻኑ ባዶ እግሩ በመንገድ ላይ ሲሄድ የተመለከቱትና ያሳሰባቸው ሰዎች ወደ ፖሊስ ደወለው መረጃ ከሰጡ በኋላ ፖሊስ ሊያገኘው እንዳቻለ ተነግሯል።
ፖሊስ በኢንስታግራም ገጽ ባሰራጨው መረጃ፤ ህጻኑ በሰዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም ብሏል።
ህጻኑ በትናንትናው እለት አባቱ ወደ ስራ መሄዱን ተከትሎ፤ የእናቱን የመኪና ቁልፍ በመያዝ "ትንሽ ዞር ብየ ልምጣ" በማለት እንደወጣም ነው የተገለጸው።
በዚህም ፖሊስ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ባደረገው እንቅስቀሴ ህጻኑ የእናቱን መኪና ለመንዳት ሲሞክር ሁለት መኪኖች መግጨቱን አረጋግጧል።
ፖሊሶቹ የመኪናው ባለቤትነት ስም በእናቱ የተመዘገበ መሆኑ ካረጋገጡ በኋላ፤ ወደ እናቱ ስልክ ደውለው ከእናቱ ጋር አገናኝተውታል።
ህጻኑ ከእናቱ ጋር በሚያወራበት ወቅት “መኪና እየነዳ እንዳለ በማስመሰል የሆነ ድምጽ ሲያሰማት ነበር”ም ብለዋል ፖሊሶቹ፡፡
የአራት አመቱ ልጅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ የቆየ ሲሆን፤ እናቱ እስክትመጣ የሚጠጣ ትኩስ ነገር እና ማጫወቻ አሻንጉሊት በመስጠት አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደተደረገለትም ፖሊስ ገልጿል።
ከዛም በኋላ ህጻኑን አደጋ ወደ ደረሰበት ቦታ ተወስዶ፤ መኪናዋ እንዴት እንደምትሰራ ከፖሊስ ለቀረበለት ጥያቄ በተግባር ማሳየቱ ፖሊሶችን አስገርሟል።
ፖሊስ ‘አስተዋይ’ እንደሆነ የሚነገርለት ልጅ “መጀመሪያ የመኪናውን በር ከፍቶ ከገባና ሞተር ካስነሳ በኋላ እግሮቹ ፍሪስዮንና ፍሬን ላይ አስቀምጧል”ም ብለዋል።
ህጻኑ ድርጊት የተደመሙ ሰዎች፤ ህጻኑ እድሜው ሲደርስ ጎበዝ የሚባል የመኪና ተወዳዳሪ ሊሆን ይችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው እየገለጹ ነው።