የቤተሰቡ አባላት አማክኝ ቁመት 2 ሜትር ከ3 ሴንቲ ሜትር ነው
የአሜሪካ ሚኔሶታ ነዋሪ የሆኑት የትራፕ ቤተሰብ በቁመታቸው ምክንያት “የዓለማችን ረጅሙ ቤተሰብ” የሚል ክብረ ወሰንን ተቀዳጅተዋል።
የቤተሰቡ አባላት አማክኝ ቁመት 2 ሜትር ከ3 ሴንቲ ሜትር መሆኑንም ኦዲቲ ሴንተራል በድረ ገጹ አስነብቧል።
የቤተሰቡ አባል የሆነችው ክሪሲ ትራፕ በዓለማችን ረጅሙ ቤተሰብ ውስጥ አጭሯ ሴት የተባለች ሲሆን፤ ቁመቷም 1 ሜትር ከ91 ሴንቲ ሜትር መሆኑ ተነገሯል።
ክሪሲ የቤተሰቡ አባል ስለሆነች አጭር ብትባለም አማካኝ የሴቶች ቁመት ሲታይ ግን ክሪሲ አንድ በጣም ረጅም ሴት የምታሟላውን መስፈርት ይዛለች።
የክሪሲ ባለቤት የሆነው ስኮት 2 ሜትር ከ2 ሴንቲሜትር የሚረዝም ሲሆን፤ የክሪሲ እና ስኮት ሁለት ሴት ልጆች የሆኑት ሳቫና እና ሞሊይ 2 ሜትር ከ3 ሴንቲ ሜትር እና 1 ሜትር ከ97 ሴንቲ ሜትር ይረዝማሉ።
የቤተሰቡ በእድሜ ትንሹ አዳም ትራፕ ደግሞ 2 ሜትር ከ21.27 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ሲሆን፤ የብተሰቡ ቁመት አንድ ላይ ሲደመርም የአንድ የሜዳ ቴን መጫወቻ ሜዳ ግመሽን የሚሸፍን ነው ተብሏል።
አዳም ትራፕ ከቤተሰቡ በጣም ረጅሙ ሲሆን፤ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ የዓለም ረጅሙ ቤተሰብ ተብሎ የመስፈር ሃሳብን ያመጣው እሱ እንደሆነ ተነግሯል።
የዓለማችን ረጅሙ ቤተሰብ ስለመሆን ሲናገሩ፣ ትራፕስ ቤተሰብ “ቁመታቸው እየጨመረ ሲመጣ አንድ አንድ ለመግለጽ ከባድ የሆኑ ህመሞች እንዳጋጠሟቸው ተናግረው በሰውነታቸው ላይ ጠባሳ ጥሎ አልፏል” ሲሉ ተናግረዋል።
ሳቫና የተባለችው የቤተሰቡ አባል ለዓለም ድነቃ ድንቅ መዝገብ እንደተናገረችው፤ አንድ ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ቁመቷ በ 1 ኢንች ከግማሽ ጨምሯል።
የትራፕ ቤተሰብ ለልብስ እና ጫማዎች ሲገዙ በልካቸው ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተናግረው፤ ሆኖም ግን ግን በጣም ረጅም መሆን ጥቅም እንዳለውም ይናገራሉ።