በጎርፍ በወደመችው ደርና ከተማ ቤተሰቦች የጠፉባቸውን ሰዎች እስካሁን እየፈለጉ ነው
በድንገት የተከሰተው ጎርፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀጠፈ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ብዙዎች ቤተሰቦቻቸውን ፈልገው ማግኘት አልቻሉም
በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች በፍጥነት እና በጅምላ መቀበራቸው በቤተሰቦቻቸው በቀላሉ እንዳይለዩ ማድረጉም ሲገለጹ ነበር
በጎርፍ ክፉኛ በተመታችው የሊቢያዋ ደርና ከተማ ቤተሰቦች የጠፉባቸውን ሰዎች እስካሁን በመፈለግ ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፈው ወር ከባድ የተባለ ጎረፍ ደርና የተባለችውን ከተማ ካወደመበት ጊዜ ጀምሮ አብዱል ሰላም አል-ካዲ አባቱን እና ወንድሙን መፈለጉን ቀጥሏል።
ካዲ በህይወት እንደማያገኛቸው ያውቃል ነገሮግን አካላቸውን አግኝቶ በመቅበር የሚያለቅሰበት መቃብር ይፈልጋል።
ካዲ ከጓደኞቹ ጋር በመሆኑን ቤታቸው የነበረበትን የጭቃ ክምር ፈነቃቀለ፤ እያንዳንዱ ሆስፒታልም ሄዶ ጠየቀ።
ካዲ አስከሬናቸው የተገኙ 4000 ሰዎችን ፎቶዎች አገላብጦ አይቷል።ነገርግን የካዲ ቤተሰቦች በውስጡ የሉም።
የ43 አመቱ ካዲ ይኖር ከነበረበት አሜሪካ ተነስቶ ደርና ለመድረስ ሁለት ቀናት ፈጅቶበታል።
" ዉሃ ወስዷቸዋል ብለን አሰብን። ምናልባትም ወደብ አካባቢ ይሆናሉ ብለን አሰብን። ይህ ቀን እጅግ አስጨናቂ ነው"ይላል።
በድንገት የተከሰተው ጎርፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀጠፈ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ብዙዎች ቤተሰቦቻቸውን ፈልገው ማግኘት አልቻሉም።
የሊቢያ ተቀናቃኝ ፖርቲዎች ለችግሩ መከሰት አንደኛው ሌላኛውን ተጠያቂ በማድረግ ላይ ናቸው።
በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች በፍጥነት እና በጅምላ መቀበራቸው በቤተሰቦቻቸው በቀላሉ እንዳይለዩ ማድረጉም ሲገለጹ ነበር።
አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችም የአደጋው ሰለባዎች በጅምላ መቀበራቸውን በመቃወም መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል።
የተወለደባትን ከተማ በቅጡ መለየት ያልቻለው ካዱ እናቱ እና እህቱ፣ አባቱ እና ወንዴሙ ይገኛሉ የሚል ተስፋ አላቸው ሲል ናግሯል።
በምስራቃዊ ሊቢያ የምትገኘው ደርና ከተማ ከተራራ በሚነሳ ወንዝ ላይ የተገነባች ነች። ከተማዋ በ2011 በኔቶ በሚደገፈው አመጽ ከፍተኛ ውድመት ማስተናገዷም ይታወሳል።
መንግስት ከተማዋን ለማደስ ቃል ገብቷል። ነገርግን ሮይተርስ ባለፈው ሳምንት አናገርኳቸው እንዳለቸው ነዋሪዎች ከሆነ ለጥገናም ሆነ ለግንባታ መንግስት ድጋፍ እንዳላደረገላቸው ገልጸዋል።
አደጋው እንዲከሰት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ የከተማው ከንቲባ ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት ታስረዋል።