በሊቢያ የተከሰተው ጎርፍ ደርና የተባለችውን ከተማ ሩብ ክፍል አወደመ
"ዳንኤል" የሚል ስያሜ የተሰጠው ማዕበል ለአስር አመት በቆየ ግጭት የተከፋፈለችውን ሀገር አጥለቅልቋል
በሊቢያ የተከሰተው ከባድ ጎርፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት የቀጠፈ ሲሆን በትንሹ 10ሺ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም
በሊቢያ የተከሰተው ከባድ ጎርፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት የቀጠፈ ሲሆን በትንሹ 10ሺ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
ድልድዮችን እና ህንጻዎችን የገነደሰው ይህ ከባድ ጎርፍ የምስራቃዊቷን ደርና ከተማ ሩብ ክፍል አውድሟል ተብሏል።
በደርና ከተማ አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሙያ ከ2000 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ነገርግን የምስራቅ ሊቢያ ባለስልጣናት 5000 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተናግረዋል።
በሜዲትራኒያን አካባቢ የተከሰተው 'ስቶርም ዳንኤል' ለአስር አመት በቆየ ግጭት የተከፋፈለችውን ሀገር አጥለቅልቋል።
ሮይተርስ 125ሺ ነዋሪዎች ያሉባት የምስራቋ ደርና ከተማ የፈራረሱ መንደሮች፣ የተደረመሱ ህንጻዎች፣ የተገለበጡ መኪናዎችን እንዲሁም የድልድይ ፍርስራሽ ማየቱን ዘግቧል።
መሀመድ አል ቃብሲ የተባለ የዋድሃ ሆስፒታል ዳይሬክተር በከተማዋ ሁለት አካባቢዎች 2300 ሰዎች መሞታቸውን ተናግሯል።
ሮይተርስም በሆስፒታል ግቢ ባሉ ኮሪደሮች ላይ አስከሬኖችን መመልከቱን ዘግቧል።