ሊቢያ የጎርፍ አደጋ የተከሰተባትን ደርና ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ባለስልጣናትን በቁጥጥር ስር አዋለች
ነዋሪዎች ለግድቦቹ መደርመስና ለአደጋው ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርገዋል
አቃቢ ህግ በተደረመሱ ግድቦች ምክንያት በስምንት ሹማምንት ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቱን አስታውቋል
በምስራቅ ሊቢያ የደርና ከተማ ከንቲባን ጨምሮ ባለስልጣናት በተደረመሱ ሁለት ግድቦች ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ባለመስራትና በቸልተኝነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንዳስታወቀው በተደረመሱ ግድቦች ምክንያት በስምንት ሹማምንት ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቷል።
በሊቢያ ከሳምንታት በፊት ሁለት ግድቦች ተደርምሰው በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በሽህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።
አቃቢ ህግ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መሀል የደርና ከንቲባና የውሃ ሀብት አስተዳደር ኃላፊው እንደሚገኙበት ማንነታቸውን ሳይጠቅስ ገልጿል።
ነዋሪዎች ለግድቦቹ መደርመስና ለአደጋው ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርገዋል።
በፈረንጆቹ 2007 ግድቦችን ለመጠገን የተሰጠው ውል ሀገሪቱ በገባችበት የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት አለመጠናቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት ተቃዋሚዎች የከንቲባ አብዱልመናን አል-ጋይቲን መኖሪያ ቤት ያቃጠሉ ሲሆን፤ አስተዳደሩም ከስራ አግዷቸዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የከተማው ምክር ቤት አባላት በሙሉ ከስራ መባረራቸው ተነግሯል።አቃቢ ህግ በተደረመሱ ግድቦች ምክንያት በስምንት ሹማምንት ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቱን አስታውቋል