መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ላይ ትችት ሰነዘረ
ስምምነቱን ለመፈጸም ከሚጠበቅበት በላይ መሄዱን የገለጸው መንግስት በጊዚያዊ አስተዳዳር በኩል "እግር የመጎተት አዝማሚያ ይታያል" ብሏል
ስምምነቱን በተሟላ መልኩ ለመፈጸም መሞከሩን የገለጸው መንግስት በጊዚያዊ አስተዳደሩ በኩል ግን ችግር መኖሩን ገልጿል
የፌደራል መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ በትግራይ ጊዚያዊ አስተደዳር ላይ ትችት ሰነዘረ።
የፌደራል መንግስት በፕሪቶሪያው የዘላቂ ተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ትችት ሰንዝሯል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት አመታት የቆየው ደምአፋሳሽ ጦርነት የተቋጨው የፌደራል መንግስት እና ህወሓት በፕሪቶሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ ጥቅምት 2015 ባደረጉት የሰላም ስምምነት ነበር።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግስት በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረው "ቁስል እንዲሽር" ረጅም እርቀት መጓዙን ገልጿል።
መንግስት የስምምነቱን መፈረም ተከትሎ የነበረውን ጥላቻ ለማስወገድ በአፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ የሚመራ የልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ መጓዙን በበጎ አንስቷል።
መንግስት እንደገለጸው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር ሲመሰረት የአመራሩን ቦታ ክልሉ እንዲወስድ የተደረገው "መሳሳብና መጓተትን ለማስቀረት" ነው ብሏል።
ከስምምነቱ በኋላ በትግራይ ባንክን፣ ቴሌኮሙኒኬሽንን እና ትራስፖርትን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ በማድረግ ኃላፊነቱን መወጣቱን መንግስት ገልጿል።
ስምምነቱን በተሟላ መልኩ ለመፈጸም መሞከሩን የገለጸው መንግስት በጊዚያዊ አስተዳደሩ በኩል ግን ችግር መኖሩን ጠቅሷል።
መንግስት በስምምነቱ አወዛጋቢ ተብለው የተጠቀሱ ቦታዎች ጉዳይ "በህገ መንግስቱ መሰረት" እልባት ለመስጠት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
ስምምነቱን ለመፈጸም ከሚጠበቅት በላይ መሄዱን የገለጸው መንግስት በጊዚያዊ አስተዳዳር በኩል "እግር የመጎተት አዝማሚያ ይታያል" ብሏል።
መንግስት ቅሬታውን በጥቅሉ ከመግለጽ ባለፈ በጊዚያዊ አስተዳደሩ በኩል አልተፈጸሙም ያላቸውን የስምምነት ነጥቦችን አልጠቀሰም።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ በዚህ ጉዳይ እስካሁን ያለው የለም።