ኤርትራ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ለአሜሪካ ምላሽ ሰጠች
ኤርትራ አሜሪካ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነቱን ለራሷ ፍላጎት እተጠቀመችበት ነው ብላለች
አሜሪካ ኤርትራ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እንዳይፈጸም እንቅፋት እየሆነች ነው ማለቷ ይታወሳል
ኤርትራ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ለአሜሪካ ምላሽ ሰጠች
በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት የነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲቆም ምክንያት የሆነው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ሞልቶታል፡፡
የስምምነቱ አንደኛ ዓመት አስመልክቶ አሜሪካ ባወጣችው መግለጫ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልወጣም ስትል ገልጻ ነበር፡፡
ዋሸንግተን በመግለጫው ላይ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ አንዳቸው የአንዳቸውን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ እና ከአላስፈላጊ ጸብ አጫሪነት ድርጊት እንዲታቀቡም አሳስቧል፡፡
የኤርትራ የመንግስት ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል በቀድሞ ስሙ ትዊተር በተሰኘው የማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ እንዳሉት አሜሪካ የኤርትራን ስም እያጠፋች ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከጸብ አጫሪነት ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሜሪካ አሳሰበች
ሚኒስትሩ አክለውም አሜሪካ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ለራሷ የዲፕሎማሲ ፍላጎት እና ጥቅም እየተጠቀመችበት እንደሆነም አክለዋል፡፡
አሜሪካ አክላም በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች ያለው ግጭት እንዳሳሰባት ገልጻ እየተፈጸሙ ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጥላቻዎች የሀገሪቱን እና አካባቢውን ወደ አለመረጋጋት የሚያስገባ ነውም ብላለች፡፡
ተበዳዮችን ማዕከል ያደረገ እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የሽግግር ፍትህ ስርዓት እንዲዘረጋም አሜሪካ አሳስባለች፡፡እውነተኛ እና አሳታፊ ብሄራዊ ውይይት እንዲደረግ አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግም አስታውቃለች፡፡