
ወ/ሮ ሌሊሴ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ሆነው ተሾሙ
ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾመዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።
በዚህ ጉባኤም ምክር ቤቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በመንግስት እጩ ሆነው የቀረቡትን ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ ሹመት በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ወይዘሮ ሌሊሴ በዳኝነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሲሆን ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው እስኪሾሙ ድረስ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በስራ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል።
ምክር ቤቱ በዳኞች ጉባኤ ተገምግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመትም አጽድቋል።
በዚህም ወይዘሮ ዛሃራ ኡመር አሊ የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለመሃላ ፈጽመዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደው ባለው 13ኛ መደበኛ ጉባኤ የአንድ የምክር ቤት አባልን ያለመከሰስ መብት እንደሚያነሳ ይጠበቃል።