የሳዑዲ አረቢያ ፍርድ ቤት በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን በ111 ዓመት እስራት ቀጣ
የሳዑዲ ዐቃቢ ህግ ከዚህም በተጨማሪ ከ28 ሚሊዮን ሪያል በላይ ቅጣት መጣሉን አስታውቋል
“የወንበዴው ቡድን” የተባሉት ወንጀለኞቹ የማታለል እና የማጭበርበር ወንጅል ፈጽመዋል ተብሏል
የሳዑዲ አረቢያ ፍርድ ቤት በገንዘብ ማጭበርበር ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ 23 ግለሰቦች፣ የንግድ ተቋማት እና የውጭ ሀገር ዜጋን ጨምሮ በ111 ዓመት እስራት እና 28 ነጥብ 6 ሚሊዮን ያህል የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ መወሰኑን ዐቃቢ ህግ አስታውቋል።
“የወንበዴው ቡድን” የተባለውና 23 ሰዎችን ያቀፈው የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀሉ አንዲት ሳዑዲያዊት ሴት እና የውጭ ሀገር ዜግነት ያለውን ባለቤቷን ያካተታል ተብሏል።
ወንጀለኞቹ በማታለል ብዙ ዜጎችን እና ነዋሪዎችን ኢላማ በማድረግ ወርቅ ፣ ነዳጅ ፣ ቅድመ ክፍያ ካርዶች እና በውጭ ህገ-ወጥ ኢንቨስትመንቶች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ማድረግ የተጠቀሙበት ህገ-ወጥ መንገድ ነው ተብሏል።
የተጎጂዎችን የባንክ ሂሳብ ቁጥር ካገኙ በኋላ በሂሳቡ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በሙሉ በሀሰተኛ ሰዎችና በንግድ ድርጅቶች ስም ወደ ሂሳባቸው በማስተላለፍ ገንዘቡን ከሳዑዲ ውጭ ያስተላልፉታል ነው የተባለው።
ዐቃቢ ህግ የቡድኑ አባላትን በገንዘብ ማጭበርበር፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሀሰተኛ ወንጀል እና በጸረ-መረጃ ወንጀሎች ህጎችን በመጣስ ክስ መስርቶባቸዋል።
የሳዑዲ ዐቃቢ ህግ በማህበራዊ የትስስር ገጹ በወንጀል ከተገኘው ገንዘብ ተመሳሳይ መጠን ያለው ገንዘብ መያዙን ገልጿል።
ጥፋተኛ ተባሉት ወንጀለኞቹ ዜግነታቸው ሳይገለጽ ቅጣቱ እንደተላለፈባቸው ተነግሯል። "በወንጀሉ የተገኘው ገንዘብ 4 የቤት ንብረቶች፣ ተሸከርካሪዎችና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ጨምሮ “ስደተኞቹ” የእስር ጊዜያቸው ካጠናቀቁ በኋላ ከአገር እንዲወጡ ተፈርዶባቸዋል” ተብሏል።