የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀቁ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት መክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን አረዳም በፈቃዳቸው ለቀዋል
አቶ ቴወድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሹመዋል
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞነም አረዳ በራሳቸው ፈቃድ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ተገለፀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ከሰዓት ባደረገው ስብሰባ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፐሬዝዳንትን መልቀቂያ ተመልክቷል።
ምክር ቤቱ ምክር ቤቱ በውሎውየፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊና ምክትላቸው አቶ ሰሎሞን አረዳ በፈቃዳቸው ከኃላፊነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ደብዳቤ ከተመለከተ በኋላም ተቀብሏል።
ምክር ቤቱ በመቀጠል ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን ምርምሮ ሹመታቸውን አጽድቋል።
በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት ከበደን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ በ3 ድምፀ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ሹመታቸውን አጽድቋል።
በተመሳሳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አበባ እምቢአለ በሙሉ ድምፅ ሹመታቸውን ያፀደቀ ሲሆን፤ ተሿሚዎችም በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።
መልቀቂያ ያስገቡት ጠቅላይ ፍርድ ቤት መክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ በፈረንጆቹ ከ2023 እስከ 2030 ላለው ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት የክርክር ፍርድ ቤት የግማሽ ጊዜ ዳኛ ሆነው መሾማቸዉ ይታወሳል
የዳኝነት ምርጫው የተካሄደው በፈረንጆቹ ህዳር 15 ቀን 2022 በኒውዮርክ በተደረገው 34ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነበር።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ25 ዓመታት በላይ የአገልግሎት ልምድ ያላቸው የህግ ባለሙያ መሆናቸውን ይነገራል።
ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና አቶ ሰለሞን አረዳ ጥቅምት 2011 ዓ.ም ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፐሬዝዳትን ተደርገው መሾማቸው አይዘነጋም።